1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምግብ ዋጋ ንረት ስጋት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 10 2004

አሜሪካና ህንድ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ብዙ ሰብል ሳይዝ በመቅረቱ አዲስ የምግብ ቀውስ ሊከተል ይችላል የሚል ስጋት አለ ። ድርቁን ተከትሎ የምግብ ዋጋ የመጨመሩ ስጋት አመዝኗል ። የምግብ ዋጋ አሁን ካለውም በላይ እንዳይንር አንዳንድ የጀርመን

https://p.dw.com/p/15qhx
Corn stalks struggling from lack of rain and a heat wave covering most of the country lie flat on the ground Monday, July 16, 2012 in Farmingdale, Ill. The nation's widest drought in decades is spreading. More than half of the continental U.S. is now in some stage of drought, and most of the rest is abnormally dry. (Foto:Seth Perlman/AP) / Eingestellt von wa
ምስል AP

አሜሪካና ህንድ በተከሰተው ድርቅ  ምክንያት ብዙ ሰብል ሳይዝ በመቅረቱ አዲስ የምግብ ቀውስ ሊከተል ይችላል የሚል ስጋት አለ  ። ድርቁን ተከትሎ የምግብ ዋጋ የመጨመሩ ስጋት አመዝኗል ። የምግብ ዋጋ አሁን ካለውም በላይ እንዳይንር አንዳንድ የጀርመን ባንኮች ከዚህ ቀደሙ ያደርጉት እንደነበረው የምግብ ዋጋ ግምት መስጠት አቁመዋል ። የጀርመኑ ኮሜርዝ ባንክ ለመሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች  እስካሁን ሲያቀርብ የነበረውን የዋጋ ግምት  ለማቆም ወስኗል ። ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ በመድረሱ ብዙ አድናቆት ተቸሮታል ። ፉድ ዋች የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነው የምግብ ጉዳዮች ተከታታይ ድርጅት የኮሜርዝ ባንክን ውሳኔ ለሌሎች መስሪያ ቤቶችም አርአያ የሚሆን እርምጃ ሲል አወድሶታል ። በአለማችን የምግብ ቀውስ እ.ጎ.አ ከ 2008 ከተከሰተ ወዲህ ባንኮች የሚያቀርቡት የዋጋ ግምት ጠንካራ ትችት እየቀረበበበት ነው ።  ባንኮችና የመሳሰሉት ተቋማት የሚሰጧቸው ግምቶች ዋጋ እያናሩ በአለም አቀፍ ደረጃም ረሃብን በማባባስ አሰተዋጽኦ በማድረግ እየተተቹ ነው ። በዚህ የተነሳም እንደ ተችቶቹ

Ein Mann mit Regenschirm gegen die brennende Sonne geht am 2. Mai 2009 ueber eine ausgedoerrte Flaeche in den Aussenbezirken von Bhubaneswar in Indien. Bundesumweltminister Norbert Roettgen hat die Staatengemeinschaft aufgefordert, Klimaschutz-Verpflichtungen nicht zu umgehen. Die Vereinbarungen von Kopenhagen muessten daher alle Laender umfassen, also auch die USA und China, forderte Roettgen. Der Minister zeigte sich ueberzeugt, dass die Klimakonferenz einen Weg zur Begrenzung der Erderwaermung auf zwei Grad beschliessen werde. (ddp images/AP Photo/Biswaranjan Rout, Archiv) +++ AP +++
ድርቅ በህንድምስል AP

ድሃው  ምግብ የመግዛት አቅም አጥቷል ። የምግብ እህል ዋጋ ግምትን ለማቆም የወሰነው ኮሜርዝ ባንክ የዋጋ ግምት የሚያስከትላቸውን ችግሮች አስመልክቶ  በባንኮች ላይ የሚሰነዘረው ወቀሳ ብዙም አላስደሰተውም ። ስለዚሁ ጉዳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ዶቼቬለ ቢጠይቅም ፈቃደኛ አልሆነም ። ፉድ ዋች የተባለው ድርጅት ባልደረባ ማርቲን ሩከር ባንኩ ዝምታ የመረጠበትን ምክንያት ያስረዳሉ ።« ኮሜርትስ ባንክ ስለ ችግሩ ነፃ ሆኖ የማይናገረው ወረታቸውን ማፍሰስ የሚፈልጉ ደንበኞቹ  ደንግጠው  ውሳኔያቸውን እንዳይቀይሩ ነው ። ስለዚህ ባንኩ የዋጋ ግምት መስጠት ያቆመበትን ምክንያት መናገር አይፈልግም ። ፍላጎታችን ችግሩ ሊባባስ ይችላል ብለው በመስጋት የዋጋ ግምት መስጠት ያቆሙ ባንኮችን በአርአያነት ማሳወቅ ነው ። »ከኮሜርዝ ባንክ በተጨማሪ የሽፓርካሰው ዴካ ባንክና የ ባድን ቩርተምበርግ ባንክ  ለምግብ ዋጋ ግምት የሚውል ገንዘብ መመደብ አቁመዋል ።  አስቀድሞ የሚሰጠው ግምት ለብዙዎች ባለወረቶች ጥሩ የንግድ መስክ ነበር ።  የምግብ ዋጋ ለመጨመሩ አንደ አንድ ምክንያት የህዝቡ ቁጥር መጨመር ነው ። ከዚህ ሌላ የተለያዩ ሰብሎች ለነዳጅ ዘይት ምርት ጥቅም ላይ መዋላቸው ለችግሩ አስተዋጽኦ በማድረግ ይጠቀሳል ።

Senior Ranger James Garratt and his dog Fly look out over Bewl Water near Lamberhurst in Kent, Tuesday January 10, 2006. A government hearing into a contested bid to replenish the drought-hit reservoir with water from a nearby river is being held today. Southern Water wants to divert 20 million litres of water from the River Medway in Kent into its Bewl Water reservoir, which is two thirds empty. Foto: Gareth Fuller / PA +++(c) dpa - Report+++
የውሃ ያጠረው የውሐ ማጠራቀሚያ በአሜሪካምስል picture alliance/dpa

አሁን አሜሪካን የተከሰተው አይነት ድርቅ የእህል ዋጋ ወደ ላይ እንዲተኮስ ሊያደርግ ይችላል ። ከሰኔ ወዲህ የአኩሪ አተር ዋጋ በ30 በመቶ የበቆሎ ደግሞ በ 50 በመቶ ጨምሯል ። አሜሪካን  ፣አኩሪ አተርና በቆሎን በብዛት ለውጭ ገበያ የምታቀርብ ሃገር ናት ። በህንድም በዝናብ እጥረት ምክንያት ብዙ ሰብል ጠፍቷል ። ምርት ባነሰ ቁጥር ዋጋ ይጨምራል ።መንግስታዊ ያልሆነው የፉድ ዋች ባልደረባ ማርቲን ሩከር እንደሚሉት አሁንም ከሁሉም በላይ የችግሩ ሰለባ የሚሆነው ድሃው ነው ።

«እጅግ በደኽዩት አገሮች ያሉ ሰዎች ከገቢያቸው 80 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆን ገንዘብ የሚያወጡት ለምግብ ነው ። እናም በትንሹም ቢሆን ዋጋ ከጨመረ ምግብ መግዛት አይችሉም ። »

የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት መዘርዝር እንደሚያስረዳው ያለፈው ወር የምግብ ዋጋ የምግብ ቀውስ ካጋጠመበት እጎአ ከ 2008 አመተ ምህረቱ ከፍ ያለ ነው ። በወቅቱ ችግሩን በ 30 ያህል ሃገራት ማረጋጋት ተችሎ ነበር ። ከዚያን ወዲህ ግን ባንኮችና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት በሚያቀርቧቸው የምግብ ዋጋ ግምቶች ምክንያት ዋጋን በማናር ይወቀሳሉ ።

A boy pulls a cow through a dry paddy field in Jamtola village, about 59 kilometers (37 miles) west of Gauhati, India, Wednesday, Aug. 23, 2006. Farmers in Assam and other parts of northeast India are facing drought like situation due to less rainfall and extreme heat this year. Assam Government has waived land tax for affected farmers and had announced special holidays for schools from Aug. 15 to 20 in view of the heat spell. (ddp images/AP Photo/ Anupam Nath)
በድርቅ የተጠቃ እርሻ በህንድምስል AP

«  አስቀድሞ የሚተነበየው የምግብ ዋጋ  ለምግብ ዋጋ ንረት 15 በመቶ አስተዋጽኦ  እንደሚያደርግ አስልተናል ።»

Welthungerhilfe የተባለው የጀርመን የረሃብ መከላከያ ድርጅት የልማት ጉዳዮች አጥኚ የራፋኤል ሽናይደር አስተያየት ነው ። ይሁንና ተመራማሪዎች አስቀድሞ የሚቀርብ የዋጋ ግምት በምግብ ዋጋ ላይ ተፅእኖ ያሳድራል በመባሉ አይስማሙም ። በዚህ የተነሳም እንደ ዶቼ ባንክ የመሳሰሉ ባንኮች የዋጋ ግምት መስጠታቸውን አላቆሙም ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዮ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ