1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምጣኔ ሀብት ወይስ የሞራል ጥያቄ

ረቡዕ፣ ጥር 19 2002

ዳቮስ ላይ የሚካሄደው የአለም የኢኮኖሚ የውይይት መድረክ ወይም በእንግሊዘኛ ምህፃሩ WEF እና በብራዚል የሚካሄደው WSF ማለትም የአለም ማህበራዊ ጊዳዮች ላይ የሚያተኩረው የውይይት መድረክ ፤ ሲታዮ ፍጹም የሚያገናኛቸው ነገር ያለ አይመስልም።

https://p.dw.com/p/LiD2
ምስል AP

ሆኖም ወሳኝ የሆኑት የመወያያ አርዕስቶቻቸው ተመሳሳይ ናቸው። ለምሳሌ ያህል የ 21ኛው ምዕተ አመት ምጣኔ ሀብት ምን ሊመስል ይገባል? እያንዳንዳቸው አገሮች ለራሳቸው አገር ብቻ ሳይሆን እንዴት አለም አቀፍ የሆኑ ውሳኔዎች ላይ መወሰን ይችላሉ? ፤ በተለይም የሰው ልጅ በሚመጡት ምዕተ አመታት ለየትኞቹ ነገሮች ነው ዋጋ መስጠት የሚገባው የሚለውን ጥያቄ ያካትታል። ባልደረባችን HELLE JEPPESEN የዘገበችውን ልደት አበበ እንደሚከተለው አቀናብራዋለች።

ስመጥር የኩባኒያ ባለቤቶች፣ ነጋዴዎች፤ የተቋማት ተጠሪዎች እና እውቅ ፖለቲከኞች የሚገናኙበት ይህ የአለም የኢኮኖሚ የውይይት መድረክ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ለ40ኛ ጊዜ በስዊዘላንድ ከተማ ዳቮስ ላይ ይሰበሰባል። በሌላ በኩል ደግሞ የአለም የኢኮኖሚ የውይይት መድረክን የሚያወግዘው፤ ለድሆች ተቆርቋሪው የአለም ማህበራዊ የውይይት መድረክ በብራዚል፥ ፖርቶ አሌግሬ በዚሁ ሰሞን ይካሄዳል። ይሄውም ለሲቪል ህብረተሰብ መብት የሚቆረቆር የድርድር መድረክ ከተቋቋመ አስረኛ አመቱን እያከበረ ነው። ውይይቱ የሚካሄድበት ቀናትም ሆን ተብሎ በተመሳሳይ ጊዜ እንዲሆን ተመርጧል።

ምንም እንኳን የአለም ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው የውይይት መድረክ እና የአለም የኢኮኖሚ የውይይት መድረክ አላማ የሚቃረን ቢመስልም፤ ሁለቱም በየፊናቸው የሚወያዩበት ርዕስ ተመሳሳይ ነው። የ WSF ተካፋዮች አለም አቀፋዊ ትስስር የማይቀር እንደሆነና በአግባብ ሁኔታ መከናወን አለበት ባዮች ናቸው። የ WEF መስራችና ሊቀመንበር የሆኑት KLAUS SCHWAB ም፤ የአለም አቀፋዊ ትስስር የምጣኔ ሀብትን የሚመለከት ብቻ እንዳልሆነ አምነውበታል።

«ዛሬ በደንብ ለተሳሰረችው አለም እውነታ ጋር እየተጋፈጥን ነው። ይህ ማለት ችግሮች ሁሉ አለማቀፋዊ ይዘት ያላቸው መሆኑ ነው። እኛ ሁላችንም እንደ አንድ አለም አቀፍ ትስስር በጋራ መቆም ወይም መስራት እንዳለብን መማር ይገባናል። ከ 40 አመት በፊት እንዴት እንደነበር ወደኋላ ተመልሼ ሳስብ ሁሉም ስለ ብሄራዊ ኩባንያው ነበር የሚያስበው፣ ዛሬ ግን ዳቮስ አለምን ባንድነት የምንመለከትበት ቦታ ነች። »

የአለም የኢኮኖሚ የውይይት መድረክ የዚህ አመቱ መሪ መፈክሮች ፦ የአለምን ይዞታ ይበልጥ ማሻሻል፣ አዳዲስ አሰራር፣ አስተሳሰብና እቅዶች የሚሉ ናቸው።

የደቡብ አፍሪቃዊው የአካባቢ እንክብካቤ ጠበቃ CORMAC CULLINAN በበኩላቸውም እንደሚሉት ስለ ምጣኔ ሀብት አዲስ ዋጋ ልንሰጠው የሚገባን ነገር እንዳለ ግልፅ ነው።

« እኔ እንደሚመስለኝ ወናው ችግር ። እኛ የተነጠልን፣ የምድር የበላዮች እና ብዙ ማግኘት የተሻለ ነው የሚል መፈክር ያለብን መሆኑ ነው። ከእንዲህ አይነቱ ማሳክር ያለብን መሆኑ ነው። ከእንዲህ አይነቱ መሳክር መውጣት አለብን። ምክንያቱም ብዙ ማግኘት የተሻለ ነው ብለህ ባመንክ ቁጥር ሊያረካህ የሚችል መጠን አይኖርም።

50 ምድር እንኳን ሊያረካን አይችልም ምክንያቱም ሁልጊዜ የበለጠ እንመኛለንና።»

የአለም ማህበራዊ ጊዳዮች ላይ የሚያተኩረው የውይይት መድረክ ከተመሰረተ ጀምሮ በአለም ዙሪያ የሚገኙ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የአጥናፋዊ ትስስር መርህ አውጋዢዎችን አንቀሳቅሷል።

የአለም ማህበራዊ ጊዳዮች የውይይት መድረክ አብይ መርህ

«ከፈለግን ሌላም አለም መፍጠር ይቻላል። » የሚል ነው። የሀሳቡ አራማጆች

አንድ አለም ሲሉ ፣ ማንኛውም ሰው እኩል የመናገር መብቱ የሚከበርበት ፣ መሬት አልባ፣ የሰራተኛ ማህበራት፣ ነባር ተወላጆች ሁሉም የሚወከሉባት አለም ማለታቸው ነው። አንድ አለም፤ ታላላቆች ብቻ የመናገር መብት የማያገኙበት፣ ስለ አጥናፋዊ ትስስር ፓለቲከኞችና የድርጅት ሀላፊዎች የማይወስኑባት አለም ማለት ነው።

ልደት አበበ/አርያም ተክሌ/ተክሌ የኋላ