1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሞስኮ ለጆርጅያ ግዛቶች እዉቅና መስጠት እና የአዉሮጻዉያን ተቃዉሞ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 22 2000

ሩስያ ለጆርጅያ ግዛት ለሆኑት ለአሃብአዝያ እና ለደቡብ ኦሴትያ ነጻነት መስጠትዋን ካሳወቀች ወዲህ ምዕራባዉያኑ አገሮች ተቃዉሞዋቸዉን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/F5xb
በጆርጅያ ጥቁር ባህር ወደብ ዛሪ አንድ እርዳታ የጫነ መርከብ እንደደረሰ የሁለቱ አገሮች ባንዲራን በማዉለብለብ ነበር አቀባበል የተደረገለትምስል AP

የሩስያዉ ፕሪዝደንት ሜድቬደቭ ትናንት ለሁለቱ ግዛቶች እዉቅና በመስጠት ፊርማቸዉን ካኖሩ በኻላ የጀርመንዋ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ወደ ኢስቶንያ ዋና ከተማ ታሊን በመጓዝ የሩስያን ዉሳኔ በጽኑ ተቃዉመዋል። በሌላ በኩል የሁለቱ ግዛት ነዋሪዎች ደስታቸዉን በሆታ በመግለጽ ላይ ናቸዉ። ከጆርጅያ ለተገነጠሉት አሃብአዝያ እና ደቡብ ኦሴትያ ሩስያ እዉቅና ከሰጠች በኻላ የሩስያዉ ፕሪዝደንት ሜድቬደቭ ሌሎችም አገሮች እዉቅና እንዲሰጡና የሩስያን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል። የጀርመንዋ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በኢስቶንያ ዋና ከተማ በታሊን ተገኝተዉ ሩስያ ያሳለፈችዉን ዉሳኔ ነቅፈዋል፥ በመቀጠል በወቅቱ ከሞስኮ ጋር ምንም አይነት ንግግር ለማድረግ እቅድ እንደሌላቸዉ ሳይጠቁሙ አላለፉም። በሌላ በኩል የአዉሮጻዉ ህብረት የፊታችን ሰኞ በካቭካዝ ስለተከሰተዉ ችግር በሚያደርገዉ አንድ ልዩ ስብሰባ የኢስላንድ እና ሊትቬንያ አገሮች በህብረቱ አንድ ድምጽ እንዲኖራቸዉ ጥረት እንደሚያድጉ ገልጸዋል። በካቭካዝ ባለዉ ችግር ምክንያት የአዉሮጻዉ ህብረት አገራት መካከል የዉሳኔ ልዩነት እዳይኖር ስጋት ላይ ጥሎአል።.

ሩስያ ለሃብአዝያ እና ለደቡብ ኦሴትያ እዉቅና የመስጠት ጉዳይ በያዝነዉ የአዉሮጻዉያኑ አመት ከየካቲት ወር እንደተነደፈ ተገልጾአል። በዚሁ ወር የቀድሞ ሴርብያ ግዛት ኮሶቮ በዩናይትድ ስቴትስ በአዉሮጻዉ ህብረት ጀርመንን ጨምሮ የነጻነት እዉቅናን ማግኘትዋ ይታወሳል። ሩስያም በአንጻሩ ለቤልግራዱ መንግስት በመቆም ከሴርቦች ፍላጎት ዉጭ ኮሶቮ እዉቅና ማግኝትዋ አስቆጥቶአት እኛም የሁለቱን የጆርጅያ ግዛቶች እዉቅና እናሰጣለን በማለት ነበር ቅሪታቸዉን ለማካካስ የተነሱት ተብሎአል፣ ዝርዝሩን አዜብ ታደሰ