የሞዛምቢክ ሠላምና የጦርነት ሥጋት
ዓርብ፣ ሰኔ 21 2005ማስታወቂያ
የቀድሞዉ የሞዛምቢክ አማፂ ቡድን የሬናሞ አባላት ናቸዉ ተብለዉ የሚጠረጠሩ ታጣቂዎች የሐገሪቱ ትልቅ አዉራ መንገድ በሚያልፍበት አካባቢ በቅርቡ የከፈቱት ጥቃት ሐገሪቱን መልሶ ከርስ በርስ ጦርነት ይዶላል የሚል ሥጋት አሳድሯል።ከየሃያ-አመት በፊት የሠላም ዉል የተፈራረሙት የሬናሞና በሥልጣን ላይ ያለዉ የፍሬሊሞ ፓርቲዎች ልዩነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ጠብ እያመራ ነዉ።የሬናሞ አባላት ናቸዉ የተባሉት ታጣቂዎች በመኪና መንገደኞችና ሾፌሮች ላይ አደጋ መጣል የጀመሩትም ጠቡን ለማርገብ የተደረገዉ ዉጥረት ከከሸፈ በኋላ ነዉ።ታዛቢዎች፥ ለጠቡ መባባስ በሥልጣን ላይ ያለዉን ፓርቲ ይወቅሳሉ።ዮሐንስ ቤክ የዘገበዉን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።
ይልማ ሐይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ