1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሠማያዊ ፓርቲ መግለጫ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 20 2008

ፓርቲዉ ቀዉሱን አስመልክቶ ዛሬ በድጋሚ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳለዉ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች የደረሱበት ሥለማይታወቅ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እስካሁን ከተጠቀሰዉ ሰማንያ-ስድት መብለጡ አይቀርም

https://p.dw.com/p/1HWGP
ፎቶ፤ ከክምችትምስል DW

[No title]

የአዲስ አበባን የተቀናቀናጀ ማስተር ፕላን በተቃወሙ ወገኞች ላይ የመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች በወሰዱት እርምጃ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ86 እንደሚበልጥ ተቃዋሚዉ የሠማያዊ ፓርቲ አስታወቀ።ፓርቲዉ ቀዉሱን አስመልክቶ ዛሬ በድጋሚ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳለዉ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች የደረሱበት ሥለማይታወቅ የሞቱት ሰዎች ቁጥር እስካሁን ከተጠቀሰዉ ሰማንያ-ስድት መብለጡ አይቀርም።ሠማያዊ ፓርቲ ቀዉሱን በተመለከተ ከሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተባብሮ መስራቱን እንደሚቀጥል አስታዉቋልም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ጋዘጣዊ መግለጫዉን ተከታትሎት ነበር።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሀመድ

ሸዋዬ ለገሠ