1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሠማያዊ ፓርቲ ዉዝግብ

ማክሰኞ፣ ጥር 10 2008

የፓርቲዉ የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ የፓርቲዉን ደንብ ጥሰዋል ያላቸዉን አራት ባለሥልጣናት ከአባልነት አባርሯል።የፓርቲዉ የሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ ባንፃሩ የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴዉን ዉሳኔ ሕገ-ወጥ በማለት ዉሳኔዉን ሽሮታል።

https://p.dw.com/p/1Hg35
Äthiopien vor der Wahl Blaue Partei Anhänger in Addis Abeba
ምስል Reuters/Tiksa Negeri

[No title]

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበር የሠማያዊ ፓርቲ መሪዎች እርስ በርስ እየተወዛገቡ ነዉ። የፓርቲዉ የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ የፓርቲዉን ደንብ ጥሰዋል ያላቸዉን አራት ባለሥልጣናት ከአባልነት አባርሯል። የፓርቲዉ የሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ ባንፃሩ የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴዉን ዉሳኔ ሕገ-ወጥ በማለት ዉሳኔዉን ሽሮታል። «ተባረሩ» ከተባሉት አንዱ የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴዉን ዉሳኔ የፓርቲዉን ትግል ለማደናቀፍ ያለመ «የግለሠቦች ሴራ» በማለት አዉግዘዉታል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሠ