የሠራተኞች ተቃውሞ በአውሮፓ
ሐሙስ፣ ኅዳር 6 2005ማስታወቂያ
የበርካታ የአውሮፓ ሃገራት ሠራተኖች ትናንት በተካሄዱ ሰልፎችና ና የሥራ ማቆም አድማዎች በየሃገራቸው የሚካሄዱ የቁጠባ እርምጃዎችን ሲቃወሙ ውለው አምሽተዋል ። በአሁኑ ጊዜ መንግሥታት የቁጠባ መርሃ ግብሩን መቀጠሉን ሲመርጡ ተቃዋሚዎች ደግሞ አሁን የተያዘው መንገድ በመተው ሥራ አጥነትን ሊቀንስ የሚችልና ማህበራዊ ዋስትና የሚያጠናክር እርምጃ እንዲወሰድ እየጠየቁ ነው ። ተንታኞች እንደሚሉት ተቃውሞ የበረታበት የቁጠባ መርሃ ግብር ከቀጠለ በአውሮፓ ማህበራዊ ቀውስና አለመረጋጋት ሊያስከትል ይችላል ። የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን ስለ ተቃውሞው ስለ መንግሥታቱ እርምጃና መፍትሄው ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ። ገበያው ትናንት የተካሄዱትን ተቃውሞዎች ስፋት በማብራራት ይጀምራል ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ