1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሠብአዊ መብት ሕግና ገቢራዊነቱ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 30 2001

ሕጉ የፀደቀበት ሥልሳኛ አመት ዘንድሮ ሲታሰብ ገቢራዊነቱ ዛሬም ማጠያየቁ ነዉ ጭንቁ።

https://p.dw.com/p/GCRv
ታሕሳስ 1941 -ጉባኤዉምስል picture-alliance/dpa

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሐገራት ታሕሳስ 1941 ያፀደቁት አለም አቀፍ ደንብ እስከዚያ ጊዜ በነበረዉ አለም አምባገነኖች ይፈፅሙት የነበረዉን ኢ-ሰብአዊ እርምጃ ለማስቆም የመጀመሪያዉ ዉሳኔ ነበር-የሆነዉ።ፓሪስ -ፈረንሳይ ተስይሞ የነበረዉ የአለም አቀፉ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ያፀደቀዉ አጠቃላይ የሰብአዊ መብት ደንብ የጀርመን ናትሴዎች በአዉሮጳ አይሁዶች ላይ ለፈፀሙት ግፍ፥ ሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ላደረሰዉ ጥፋት መልስ፥ ለሰዉ ልጅ መብት መከበር ደግሞ ፅኑ መሰረት ነዉ።ሕጉ የፀደቀበት ሥልሳኛ አመት ዘንድሮ ሲታሰብ ገቢራዊነቱ ዛሬም ማጠያየቁ ነዉ ጭንቁ።ኡልሪከ ማስት-ኪርሽኒንግ የዘገበችዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።