1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሠብአዊ ምክር ቤት አሠራርና ዉዝግብ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 6 2009

አምባሳደር ሐሌ ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር በተለይ ቬኑዙዌላ የምክር ቤቱ አባል መሆንዋ ተገቢ እንዳልሆነ አስታዉቀዋል።የመብት ተሟጋቾች ግን ዩናይትድ ስቴትስ በሰብአዊ መብት ረጋጭነታቸዉ የሚታወቁ መንግሥታትን እየደገፈች፤ አምባሳደሯ ዓለም አቀፉን ድርጅት መዉቀሳቸዉ «ጥፋት ወይስ ልማት?» በማለት ይጠይቃሉ

https://p.dw.com/p/2eQ5Q
UN Flagge
ምስል picture-alliance/dpa

(Beri.Brussels) US-UNHRC - MP3-Stereo

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ወይዘሮ ኒኪ ሐሌይ በዓለም አቀፉ ድርጅት፤ በተለይም በድርጅቱ የሠብአዊ መብት ምክር ቤት ላይ የሠነዘሩት ትችት፤ አፀፋ ትችትና ወቀሳ ገጥሞታል።አምባሳደር ሐሌይ ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር በተለይ ቬኑዙዌላ የምክር ቤቱ አባል መሆንዋ ተገቢ እንዳልሆነ አስታዉቀዋል።የመብት ተሟጋቾች ግን ዩናይትድ ስቴትስ በሰብአዊ መብት ረጋጭነታቸዉ የሚታወቁ መንግሥታትን እየደገፈች፤ አምባሳደሯ ዓለም አቀፉን ድርጅት መዉቀሳቸዉ «ጥፋት ወይስ ልማት?» በማለት ይጠይቃሉ። የብራስልሱ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ