1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የረመዳ ፆም እና የኢድ በዓል በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ግንቦት 16 2012

ኢድ አልፈጥር ሲከበር የአዲስ አበባ ስታዲየም በእስልምና እምነት ተከታዮች ይሞላል። ረመዳንን የፆሙ በጋራ ይጸልያሉ። ዘንድሮ ግን እንደዚያ አልሆነም። በመላው ዓለም የሚገኙ የእስልምና ዕመት ተከታዮች የኢድ በዓልን እያከበሩ ነው። በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ በቤታቸው ለመቆየት ተገደዋል።

https://p.dw.com/p/3chPl
Äthiopien Bahir Dar Muslime feiern Eid Al-Fitr
ምስል DW/A. Mekonen

የረመዳ ፆም እና የኢድ በዓል በኢትዮጵያ

በመላው ዓለም የሚገኙ የእስልምና ዕመት ተከታዮች የኢድ በዓልን እያከበሩ ነው። ኢድ በእምነቱ ተከታዮች ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላት አንዱ ቢሆንም የዘንድሮው እንደ ወትሮው አይደለም። በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ በቤታቸው ለመቆየት ተገደዋል። ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ፣ መጠየቅ፣ ከቦታ ቦታ መጓጓዝ፣ በርከት ብሎ መሰብሰብ እንደወትሮው አልተሳካም።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ኢትዮጵያውያን በዓሉን እንዴት እያከበሩ ነው ሲል የተወሰኑ ሰዎች አነጋግሯል።