1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የቆሼ መንደር ነዋሪዎች ጥያቄና እየተሰበሰበ ያለዉ ርዳታ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 12 2009

አዲስ አበባ ረጲ አካባቢ በተለምዶ ቆሼ በሚባለዉ የቆሻሻ ክምር አደጋ ለተጎዱ ሠዎች በሃገር ዉስጥም ሆነ በዉጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የሚሰበሰበዉ የርዳታ ገንዘብ እንደቀጠለ ነዉ።  ከአደጋ የተረፉና ቤተሰቦቻቸዉን እና መኖርያ ቤታቸዉን ያጡ ነዋሪዎች ርዳታዉ አሁንም እንዳልደረሳቸዉ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2Zg5M
Äthiopien Erdrutsch in einer Mülldeponie in Addis Abeba
ምስል DW/Y. G. Egziabher

Müllkippe Opfer Hilfe_ Beschwerde_Addis Abeba** - MP3-Stereo

 

አዲስ አበባ ረጲ አካባቢ በተለምዶ ቆሼ በሚባለዉ የቆሻሻ ክምር አደጋ ለተጎዱ ሠዎች በሃገር ዉስጥም ሆነ በዉጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የሚሰበሰበዉ የርዳታ ገንዘብ እንደቀጠለ ነዉ።  ከአደጋ የተረፉና ቤተሰቦቻቸዉን እና መኖርያ ቤታቸዉን ያጡ ነዋሪዎች ርዳታዉ አሁንም እንዳልደረሳቸዉ ተናግረዋል። እንድያም ሆኖ የመኖርያ ቤት ለመስራት ቦታ እዩ እንደተባሉና እንዳዩ ለስብሰባም እንደተጠሩ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ በኮልፊ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸዉ ለተጎጂዎች ከመንግሥትም ሆነ ከሕዝቡ የሚደርሰዉ ርዳታ ለተጎጅዎች እየደረሰ መሆኑን መጠለያም መሰጠቱን ተናግረዋል ።

ስድስት የቤተሰብ አባላትን ያጡት ረጲ አካባቢ በተለምዶ ቆሼ በሚባለዉ አካባቢ ይኖሩ የነበሩትና በደረሰዉ አደጋ ስድስት የቤተሰቦቻቸዉን አባላት የተነጠቁት ነዋሪ አቶ አስረስ እንደተናገሩት የርዳታ ብር ቢሰበሰብም ያገተሰጠን ነገር ግን የለም ዛሬ መንግሥት የመኖርያ ቤት ለመስራት መንግሥት ለስብሰባ ጠርቶን ነበር።

« ብር ይሰበሰባል የተጎጂ ቤተሰብ እንዳለን ነዉ። ዛሬ በቀበሌ በኩል መንግሥት ሰብስቦን ነበር፤ ቦታ ምረጡ ተባለ ለአስራ ስድስት ቤተሰብ ማለት አባወራዎች ቦታ መርጠን ቦታ ይሰጣችኋላ አንድ አንድ ሚሊዮን ብር እንደሚሰጠን ተነግሮናል።አየር ጤና እና ጀሞ የሚባል ሰፈር ነዉ ቦታ እንድናይ የተጠየቅነዉ፤ ሄደን አይተናል። »     

የኮልፊ ቀራንዮ ሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተስፋዬ ለረጲ ሰፈር ጉዳተኞች  መጠለያ ተሰጥዋቸዉ ከቦታዉ ላይ አልነሳም ያሉትም ነዋሪዎች ለጊዜዉ ቦታዉ ላይ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ስድስት የቤተሰን ዓባላትን የተነጠቁት አቶ አስረስ የአዲስ አበባ ነዋሪ ለሚያደርገዉ ያላሰለሰ ድጋፍ በተደጋጋሚ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል ።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ