1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሩሲያ ጋዝ ወደ ጀርመን የሚፈስበት ቧምቧ ዉዝግብ እልባት አገኘ

ነጋሽ መሐመድ
ዓርብ፣ የካቲት 1 2011

የሩሲያ ጋዝ ወደ ጀርመን የሚፈስበት ቧምቧን በመዘርጋት፣መከታተልና መቆጣጠር ሰበብ በአዉሮጳ ሕብረት አባል መንግሥታት መካከል ተፈጥሮ የነበረዉ አለመግባባት ተወገደ።ከሩሲያ ወደ ጀርመን ከዚያም ወደ ሌሎች የአዉሮጳ ሐገራት ጋዝ የሚከፋፈልበትን ቧምቧ የመዘርጋቱ ዉል የሕብረቱን አባል መንግስታት በተለይም ጀርመንና ፈረንሳይን ሲያወዛግብ ነበር።

https://p.dw.com/p/3D2AA
Erdgaspipeline Eugal wird im Nordosten verlegt
ምስል picture-alliance/dpa/S. Sauer

የሩሲያ ጋዝ ወደ ጀርመን የሚፈስበት ቧምቧን በመዘርጋት፣መከታተልና መቆጣጠር ሰበብ በአዉሮጳ ሕብረት አባል መንግሥታት መካከል ተፈጥሮ የነበረዉ አለመግባባት ተወገደ።ከሩሲያ ወደ ጀርመን ከዚያም ወደ ሌሎች የአዉሮጳ ሐገራት ጋዝ የሚከፋፈልበትን ቧምቧ የመዘርጋቱ ዉል የሕብረቱን አባል መንግስታት በተለይም ጀርመንና ፈረንሳይን ሲያወዛግብ ነበር። ዉዝግቡን ለማስወገድ የአባል መንግስታት ተወካዮች በተከታታይ ሲደራደሩ ነበር።የጀርመንዋ መራሒተ መንግስት ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ዛሬ እንዳስታወቁት ፈረንሳይና ጀርመን በመስማማታቸዉ ዉዝግቡ ተወግዷል።«የጋዙን መመሪያ በተመለከተ ከስምምነት ላይ ደርሰናል።ስምምነት ማድረግ የተቻለዉ ጀርመን ፈረንሳይ በቅርብ ተባብረዉ በመስራታቸዉ ነዉ።ጀርመን ከተለያዩ ምንጮች ኃይል የማግኘት መብቷን ማስከበር ትፈልጋለች።ሩሲያ ከነዚሕ ምንጮች አንዷ ናት።ብቸኛዋ ግን አይደለችም።እዚሑ ጀርመን ዉስጥም ፈሳሽ ጋዝ እናጠራቅማለን።»
አዲስ በተደረገዉ ስምምነት መሠረት ቦልቲክን አቋርጦ ጀርመን የሚደርሰዉን የጋዝ ቧምቧ የሚያስተዳድረዉ የሩሲያዉ ኩባንያ ጋዝፕሮም ለአዉሮጳ ሕብረት መመሪያና ደንቦች ተገዢ ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ወደፊት በሚወስነዉ መሰረት የስምምነቱ ዝርዝር አፈፃፀም ይፋ ይሆናል።

Slowakei Bratislawa Visegrad Treffen | Angela Merkel
ምስል Reuters/D. W. Cerny

 

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ