የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚደንት ሪየክ ማቸር ከሀገር መሸሽ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 12 2008ማስታወቂያ
ካለፈው ሚያዝያ እስካለፈው ሀምሌ ወር አጋማሽ የሽግግሩ መንግሥት ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው የሰሩት ማቸር የሸሹት ከተቀናቃኞቻቸው የደቡብ ሱዳን መንግሥት ጦር ክትትል ስላረፈባቸው መሆኑን ቃል አቀባዩ አመልክተዋል። ማቻር በአሁኑ ጊዜ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሬፐብሊክ መዲና ኪንሻሳ መግባታቸውንም ቃል አቀባዩ አክለው አስታውቀዋል። የሪየክ ማቸር ከደቡብ ሱዳን መሸሽ በሀገሪቱ ጊዚያዊ ሁኔታ ላይ ምን አንደምታ ይኖረዋል? የናይሮቢ ወኪላችንን ፋሲል ግርማን አነጋግሬዋለሁ።
ፋሲል ግርማ
አርይም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ