1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የራስሙሰን ጋዜጣዊ መግለጫ

ሰኞ፣ ሐምሌ 27 2001

አዲሱ የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ዋና ፀሀፊ አንደርስ ፎህ ራስሙሰን በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ድርጅታቸው ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ይፋ አድርገዋል ።

https://p.dw.com/p/J2tB
አዲሱ የኔቶ ዋና ፀሀፊ አንደርስ ፎህ ራስሙሰንምስል picture-alliance/ dpa

ራስሙሰን የድርጅቱን ዋና ፀሀፊነት ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት አፍጋኒስታን የኔቶና የሩስያ እንዲሁም የኔቶና የሜዲቴራንያን አካባቢ አገራት ግንኙነት ድርጅታቸው በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ዋነኛዎቹ ናቸው ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል ፣ ሂሩት መለሰ፣ ተክሌ የኋላ