1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የራስ መከላከል ጥበብ ስልጠናዎች

ዓርብ፣ ጥር 30 2006

እንደ ጁዶ እና ሌሎች ተመሳሳይ የራስ መከላከል ስፖርታዊ ጥበቦች ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙም የተለመዱ አይደሉም። ሆኖም ጀርመን ነዋሪ የሆኑት ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ ወደ ኢትዮጲያ ሄደው በዚህ ስፖርት ወጣቶችን ማሰልጠን ከጀመሩ አንስቶ አንዳንድ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ሳይቀር ተሰልፈው የሚወዳደሩ ወጣት ኢትዮጵያውያንን ማፍራት እንደተቻለ ገልፀውልናል።

https://p.dw.com/p/1B3J7
Symbolbild Judo
ምስል Fotolia/vekha

ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ በዚህ በጀርመን ሀገር የኢኮኖሚ ባለሙያ ናቸው። ማርሻል አርት በመባል የሚታወቀው የራስ መከላከል ጥበብ ካለፉት 24 ዓመት ጀምሮ አልተለያቸውም። ዶክተር ፀጋዬ የአፍሪቃ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ይህንን ስፖርትም በኢትዮጵያ ካለፉት 6 ዓመታት አንስቶ ያስፋፉ ባለሙያ ናቸው።

ያሬድ ንጉሴ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰልጥኖ ፣ ሌሎችን ለማሰልጠን የበቃ ወጣት ነው። ወጣቱ ብረታ ብረቶችን በመበየድ በግል ሥራ ይተዳደራል።

ያሬድ በስፖርቱ ገፍቶበት በኦስትሪያ በተካሄደ ውድድር ላይ የመካፈል እድል አግኝቷል። በእንደዚህ አይነት የዓለም አቀፍ ውድድሮች ሲካፈል የመጀመሪያ ጊዜ ነው። ወደፊትም ገፍቶበት እንደሚሰራ ገልጾልናል።

በዚህ ስፖርት ከተሳተፉ ጥቂት ሴቶች አንዷ የ17 ዓመቷ ሃና መሪ ናት። ሃና የሒሳብ አያያዝ ተማሪ ስትሆን በትርፍ ጊዜዋ ጁዶ እና ሌሎች ተመሳሳይ ስፖርቶችንም ትለማመዳለች። ሃና ስፖርቱ ህይወቷን በምን መልኩ እንደለወጠው እና ሌሎችም አጫውታናለች።

ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙም ስላልተለመዱት እንደ ጁዶ ያሉ የራስ መከላከል ጥበቦች ስልጠና እና ተሳትፎ ከዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ሙሉ የድምፅ ዘገባ ያገኛሉ።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ