1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የራእይ ፓርቲ የመግባባትና ዕርቅ መርኀግብር

ሐሙስ፣ ሐምሌ 18 2005

የኢትዮጵያ ራእይ ፓርቲ ፤ በሀገሪቱ ሊያካሂድ ያሰበውን ፤ ያስፈልጋል ብሎ ያመነበትን የብሔራዊ መግባባትና ዕርቅ ያለውን መርኀ ግብር በዛሬው ዕለት ይፋ ማድረጉን የአዲስ አበባው ዘጋቢአችን ፣ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

https://p.dw.com/p/19EMY

ፓርቲው ይፋ ባደረገው፤ የብሔራዊ መግብብትና ዕርቅ መርኀ ግብር ፣ ቀጣይ እንቅሥቃሴው፤ መርኀ ግብሩን በሚዳስሱ ጥናታዊ ጽሑፎች ላይ ውይይት እንዲካሄድ ማድረግን ፣ህዝባዊ ስብሰባዎችን ሰላማዊ ሰልፍ ማድረን እንዲሁም የእግር ጉዞን ያካትታል። 9 ነጥቦችን ያካተተውን የጽሑፍ መግለጫ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሠብሮ እንደሚከተለው ነበረ ፤ ለዘጋቢአችን ጠቅለል አድረገው ያብራሩለት።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ