1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የርዋንዳ ዓማፅያን መሪ እጃቸውን መስጠት

ዓርብ፣ ኅዳር 11 1996
https://p.dw.com/p/E0lH
ወግ አጥባቂው ዕለታዊ ፍራንክፉርተር ጋዜጣ ባቀረበው ዘገባው፡ የርዋንዳ ሕዝብ፡ የርዋንዳ ዓማፅያን እንቅስቃሴ፡ በምሕፃሩ ኤፍ ዲ ኤል አር መሪ ጀነራል ፖል ርዋራካቢየ ባለፈው የሣምንት መጨረሻ እጃቸውን ለርዋንዳ ጦር በሰጡበት ድርጊት በርዋንዳ መንግሥትና እአአ ለ 1994 ዓም የጎሣ ጭፍጨፋ ተጠያቂ በሆኑት አክራሪ የሑቱ የኢንተራሃምዌ ዓማፅያን መካከል የሚካሄደውን ውጊያ ፍፃሜ ያስገኛል በሚል ተሳ አድርጓል። ርዋንዳ ርዋራካቢየ ከመሩት ከኮንጎ ከተነሳቀሰው ከኢንተራሃምዌ ሚሊሺያዎችና ከጎሣው ጭፍጨፋ በኋላ ወደ ኮንጎ ከሸሹት የቀድሞ የርዋንዳ ጦር አባላት ከተውጣጣው ያማፅያን ቡድን የሚሰነዘርባትን ጥቃት ራስዋን ለመከላከል ብቻ ስትል ባለፉት ዓመታት በኮንጎ ውዝግብ የጦር ጣልቃ ገብነት ማድረጓን በተደጋጋሚ ማስታወቋ የሚታወስ ነው። ርዋራካቢየ ወደ ኮንጎ ከመሸሻቸው በፊት በርዋንዳ ጦር ውስጥ ቢያገለግሉም፡ የርዋንዳን የጦር ወንጀል እንዲመለከት በአሩሻ፡ ታንዛንያ በተቋቋመው ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ክስ አልተመሠረተባቸውም። በዚህም የተነሣ፡ ይላል ፍራንክፉርተር አልገማይነ ጋዜጣ፡ በኮንጎ የሚገኙት ቀሪዎቹ የርዋራካቢየ ተከታዮች ለርዋንዳ ጦር እጃቸውን እንዲሰጡ ትጠብቃለች። ይኸው ትፅቢትዋም የኮንጎ መንግሥት የሀገሩን ውዝግብ ለማብቃት የተዘጋጀውን የሰላም ውል በፈረመበት ድርጊት ሀገድ እንደሚሆን ነው የሚገመተው፤ ምክንያቱም፡ በሰላሙ ውል መሠረት የኮንጎ መንግሥት በርዋንዳ አንፃር ከሀገሩ ለተንቀሳቀሱት የሑቱ ዓማፃያን ይሰጠው የነበረውን ድጋፍ የማቋረጥ ግዴታ አለበት።