1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የርዕሰ ሊቃነ-ጳጳሳቱ የአረብ ኤሜሪትን ጉበኙ

ማክሰኞ፣ ጥር 28 2011

በተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ ጉብኝት ላይ የሚገኙት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በጉዞአቸዉ ማጠናቀቅያ አቡዳቢ በሚገኝ ስታድዮም በተካሄደ ደማቅ ሃይማኖታዊ ስነስርዓት ተካፈሉ።

https://p.dw.com/p/3CmB7
Papst Franziskus in Abu Dhabi
ምስል Reuters/Handout Vatican Media

በተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ ጉብኝት ላይ የሚገኙት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በጉዞአቸዉ ማጠናቀቅያ አቡዳቢ በሚገኝ ስታድዮም በተካሄደ ደማቅ ሃይማኖታዊ ስነስርዓት ተካፈሉ። በአብዛኛዉ ሙስሊም ማኅበረሰብ በሚገኝበት ሃገር አንድ የካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ይህን መሰል ሃይማኖታዊ መርሃ ግብር ሲያካሂድ ለመጀመርያ ጊዜነዉም ተብሎአል። አንድ የቫቲካን ዜና ወኪል እንደዘገበዉ ከሆነ በበስነ ስርዓቱ ላይ 135 ሺህ ሰዎች ተካፋይ ነበሩ፤ ከመካከላቸው 4 ሺዉ ሙስሊሞች መሆናቸዉ ተዘግቧል። ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሥነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር በተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ የሚገኙ ክርስትያኖች አብዛኞቹ  ከሌሎች ሃገሮች ለሥራ የመጡ በመሆናቸዉ ከቤተሰቦቻቸዉ ተለይተዉ መኖራቸዉ ሁኔታዉ ለነሱ ቀላል አይደለም ብለዋል። በተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ ካለው ነዋሪ 80 በመቶዉየውጭ ዜጋ ነዉ። 

 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ