1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና የቅዱሳን ስያሜ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 20 2006

በትናንትናዉ ዕለት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሁለት ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳትን የቅድስና ሥርዓት አካሂዳለች። በቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱሳን የተባሉት ዮሐንስ 23ኛ እና ዮሐንስ ጳዉሎስ ዳግማዊ የተባሉት በርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳትነት ያገለገሉ አባቶች ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/1BqR9
ምስል ALBERTO PIZZOLI/AFP/Getty Images

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የሁለቱን ቀደምት የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶች ቅድስና ይፋ ያደረጉት በመቶ ሺዎች የሚገመቱ የዕምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ነዉ። በወቅቱም በሕይወት እያሉ መንበሩን የለቀቁት ቤኔዲክት 16ኛና በርካታ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም የተጋበዙ እንግዶች በተገኙበት ለየት ያለዉን ሥርዓት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ መርተዋል። ይህንንም በቅዱስ ጴጥሮስ ወጳዉሎስ አደባባይ ቫቲካን የተገኙ ብቻ ሳይሆኑ በርካቶች በየሚገኙበት በቴሌቪዥን አማካኝነት መከታተላቸዉን የሮሙ ዘጋቢያችን ተኽለእዝጊ ገብረ ኢየሱስ በላከልን ዘገባ ጠቅሷል።

ተኽለእዝጊ ገብረ ኢየሱስ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ