1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሮቢንሠን መታሠቢያ ማዕከል

ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 2008

ኮሎኔል ሮበንሰን ኢትዮጵያ በፋሽስት ኢጣሊያ በተወረረችበት ወቅት ወረራዉን በመቃወም የኢትዮጵያ አርበኖችን መርዳታቸዉም እየተነገረ ነዉ

https://p.dw.com/p/1IlFQ
Eröffnung des amerikanischen Kulturzentrums in Addis
ምስል DW/G.T.Haile-Giorgis

[No title]

የኢትዮጵያን አየር ሐይል እና አየር መንገድ የመጀመሪያ ፓይለቶችን ላሠለጡት አፍሮ-አሜሪካዊዉ ፓይለት ለኮሎኔል ጆን ቻርልስ ሮብንሰን መታሠሚያ አዲስ አበባ ዉስጥ የተዘጋጀዉ ማዕከል ተመረቀ።በብሔራዊ ቤተ-መዛግብት እና ቤተ-መፀሐፍት ድርጅት የተዘጋጀዉ ማዕከል ለምርምርና ጥናት ያገለግላል ተብሏል።ኮሎኔል ሮበንሰን ኢትዮጵያ በፋሽስት ኢጣሊያ በተወረረችበት ወቅት ወረራዉን በመቃወም የኢትዮጵያ አርበኖችን መርዳታቸዉም እየተነገረ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ እንደዘገበዉ ኮሎኔሉ በጦርነቱ መሳተፍ አለመሳተፋቸዉ ገና በጥናት አልተረጋገጠም።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ