1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰለጠነ የሰው ኃይል ዕጥረት በጀርመን

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 4 2002

ከዛሬ ሁለት ዓመተ በፊት የዓለምን ቀልብ በእጅጉ በሳበው የዓለም የገንዘብ ቀውስ ሰበብ በአውሮፓ የህዝብ ቁጥር መናመንና የሰለጠነ የሰው ኃይል ዕጥረት እንደ በፊቱ ትኩረት ሊሰጠው አልቻለም ።

https://p.dw.com/p/Ohqw
የሰለጠነ የሰው ኃይል ዕጥረት በጀርመን
ምስል picture-alliance/dpa

የስራ አጡ ቁጥር ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት ላይ ከአሁን ወዲያ በተለይ ልዩ ሙያ ያላቸው ሰራተኞች ዕጥረት ይኖራል የሚል ግምት አልነበረም ። ይሁንና ዕውነታው ግን ከዚህ የተለየ ሆኗል ። በአብዛኛዎቹ የአውሮፓ ኢንዱስትሪዎች ባላቀ ደረጃ የሰለጠኑ ባለሞያዎች ዕጥረት አሁንም ትልቅ ራስ ምታት እንደሆነ የዘለቀ ጉዳይ ነው ። እስካሁን መፍትሄ ተብለው የተወሰዱት ዕርምጃዎችም የዶይቼቬለው ዲርክ ካውፍማን እንደዘገበው በጀርመንም ጭምር ለውጥ አላስገኙም ። የዛሬው አውሮፓ ጀርመን የሚያተኩርበት ርዕሰ ጉዳይ ነው ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ