1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ሴቶች

ዓርብ፣ መስከረም 26 2004

የዘንድሮዉ የሰላም ኖቤል ተሸላሚዎች ሶስት ሴቶች መሆናቸዉን የሽልማት ሰጪዉ ተቋም ያሳታወቀዉ በአዉሮጳ ከእኩለ ቀን በፊት ነዉ።

https://p.dw.com/p/Rpqg
ምስል dapd/DW-Montage

ከተሸላሚዎቹ ሁለቱ ላይቤሪያዉያን፤ አንድዋ ደግሞ የመናዊት ስትሆን ለዚህ ክብር ያበቃቸዉ ለሴቶች መብት መታገላቸዉና ሰላምን ለመገንባት ባደረጉት አስተዋፅኦ እንደሆነ የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ ሊቀመንበር ገልጸዋል። የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሴቶችን መብት ለመከላከል ለሚጥሩ ሶስት ሴቶች የሰላም ኖቤል ሽልማቱ መሰጠቱ በዓለም ሰላማዊ ማኅበረሰብ ለመገንባትና ፍትሃዊነትን ለማስፈን መሠረት ነዉ ሲል አወድሶታል። በዘንድሮዉ ሽልማት ሁለት አፍሪቃዉያን መካተታቸዉ አህጉሪቱ ያሏትን የኖቤል ተሸላሚዎች ቁጥር ወደ16 ከፍ አድርጎታል። እንዲያም ሆኖ በሴቶች ረገድ የነበሯት አንዲት የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ኬንያዊቷ የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪ፤ የዛፎች እናት በመባል የሚታወቁት ፕሮፌሰር ዋንጋሪ ማታይን ሰሞኑን ማጣቷ ይታወቃል። ማታይ ከነክብራቸዉ ቢያልፉም ሌሎች ጠንካራ ሴቶችን በእግራቸዉ ተክተዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ