1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰማያዊ አባላት ፍርድ ቤት ሲለቃቸዉ ፖሊስ ያዛቸዉ

ሐሙስ፣ ሰኔ 18 2007

ባለፈዉ መንግሥት ራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለዉን በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ IS የተሰኘዉን ቡድን ለመቃወም በጠራዉ ሰልፍ ላይ አመፅ አነሳስታችኋል የተባሉ አምስት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ፍርድ ቤት ቀርበዉ ቢለቀቁም ፖሊስ መልሶ እንዳሰራቸዉ ፓርቲዉ አመለከተ።

https://p.dw.com/p/1FnOu
Demonstration der Semayawi-Partei in Addis Ababa Äthiopien 22.09.2013
ምስል DW

አባላቱ ዳግም ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ዳኞች እንዲፈቱ መወሰናቸዉን በድጋሚ ቢያሳዉቁም ፖሊስ ግን አሁንም ሊለቃቸዉ ፈቃደኛ አለመሆኑን የፓርቲዉ ሊቀመንበር ለዶይቬ ቬለ ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ደብረማርቆስ ከተማ ላይ የተገደለዉ አባላቸዉን ቤተሰቦች ለማፅናናት የተንቀሳቀሰዉ የሰማያዊ ፓርቲ የልዑካን ቡድን የጎሀ ጽዮን ፖሊስ ካሜራቸዉን ቀምቶ እንዲመለሱ ማድረጉም ታዉቋል። ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል፤

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ