1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 14 2010

ሰማያዊ ፓርቲ ዘርን መሰረት ያደረገ ነው የሚለውን የዜጎች መፈናቀልን እንዲያስቆም ለኢትዮጵያ መንግሥት ጠንካራ ማሳሰቢያ አቀረበ። ፓርቲው ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጠው መግለጫው፣ መንግሥት ለዜጎች መፈናቀል ተጠያቂ የሚባሉትንም ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቆ፣ ይህን ካላደረገ ግን አገር አቀፍ የህዝብ ንቅናቄ እንደሚጠራ ግልጽ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/2y7xa
Demonstration der Semayawi-Partei in Addis Ababa Äthiopien 22.09.2013
ምስል DW

ሰማያዊ ፓርቲ መንግሥት ለዜጎች መፈናቀል ተጠያቂ የሚባሉትን ለፍርድ ካላቀረበ አገር አቀፍ የሕዝብ ንቅናቄ እጠራለሁ አለ።

ፓርቲው ከገዚው ፓርቲ ለቀረበለት የእንደራደር ጥያቄም፣ ድርድሩ በገለልተኛ ወገን አደራዳሪነት እስከተካሄደ እና ሁሉንም ይመለከተናል የሚሉ ወገኖችን፣ ሰላማዊ እና የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱትንም ሳይቀር የሚያሳትፍ እስከሆነ ድረስ ፈቃደኛ መሆኑን በመግለጽ ምላሽ መስጠቱን አስታውቋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ