1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰማያዊ ፓርቲ ሮሮና የምርጫ ቦርድ መልስ

ረቡዕ፣ መጋቢት 30 2007

ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም በነዚህ እጩዎች ላይ የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ከእጩነት ቢያገላቸውም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶ እንዲወዳደሩ እንደተበየነለት ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/1F4Gc
Büro des National Electoral Board of Ethiopia NEBE
ምስል DW


የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበር ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ ያገዳቸው 15 ተወዳዳሪዎቹ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በአማራ ክልል በዕጩነት እንዲመለሱ ውሳኔ ቢሰጥም የእጩነት መታወቂያ ተነፍጓቸዋል ሲል አማረረ ።ፓርቲው እንዳስታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለማክበር ለእጩዎቹ መታወቂያ አልሰጠም ። ምርጫ ቦርድ ከዚህ ቀደም በነዚህ እጩዎች ላይ የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ከእጩነት ቢያገላቸውም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶ እንዲወዳደሩ እንደተበየነለት ፓርቲው አስታውቋል ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ፍርድ ቤት እገዳው እንዲነሳላቸው ውሳኔ የሰጠው ለ3 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እንደሆነና ይህንኑም ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል ።ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ልኮልናል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ