1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቃጠሎ አልቆመም

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 5 2011

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ወደ 400 ሔክታር መሬት አጥፍቷል። ቃጠሎው ዋልያና ጭላዳ ዝንጀሮ በሚገኙባቸው የፓርኩ ክፍሎች መድረሱን ወደ ቦታው የተጓዘው የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ ተናግሯል። በባሌ እና ሀላይደጌ አሰቦት ተመሳሳይ ቃጠሎ ደርሶ የዜጎችን ትብብር ለመለመን የተገደደችው ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሐብቷን መታደግ ለምን ተሳናት?

https://p.dw.com/p/3GjV8
Bildergalerie Rote Liste des gefährdeten Welterbes (Nationalpark Simien)
ምስል picture alliance/Robert Harding

የዶይቼ ቬለው ዘጋቢ የሰሜን ተራሮች ፓርክ ቅኝት

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ላይ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ወደ 400 ሔክታር መሬት አጥፍቷል። የእሳት ቃጠሎው በተለይ ዋልያ እና ጭላዳ ዝንጀሮ በሚገኙባቸው የፓርኩ ክፍሎች መድረሱን ወደ ቦታው የተጓዘው ሰለሞን ሙጬ ዘግቧል። አስታ እና ወጨኒ የተባሉ የዛፍ አይነቶች፤ የጓሳ ምድር፤ የወፍ ጎጆዎች እና የአይጥ ዝርያዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የአማራ ክልል እና የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ባለሥልጣናት የእሳት ቃጠሎውን መቆጣጠር እንዳልተቻለ ወደ ቦታው ላቀናው የጋዜጠኞች ቡድን ተናግረዋል። ከደቡብ አፍሪቃ ወይም ከኬንያ በውሰት ይመጣሉ የተባሉት የእሳት ማጥፊያ ሔሊኮፕተሮች ጉዳይ ገና መቋጫ አላገኘም።

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ባለፈው መጋቢት 19 በተመሳሳይ ሁኔታ የተነሳው እሳት ለሳምንት ያህል ቆይቶ ጠፍቷል። በወቅቱም ከ342 ሄክታር በላይ የፓርኩ ክፍል መቃጠሉን ኃላፊዎች ገልጸው ነበር፡፡ በፓርኩ ላይ የእሳት ቃጠሎው እንደገና ያገረሸው ባለፈው ሰኞ መጋቢት 30 አመሻሽ ላይ ነው። 

በዚህ አመት ብቻ የባሌ ብሔራዊ ፓርክ፤ ሀላይደጌ አሰቦት ብሔራዊ ፓርክ ተመሳሳይ ቃጠሎ ደርሶባቸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲህ አይነቱን ቃጠሎ አስቀድሞ ለመከላከል ሆነ ለማጥፋት የዜጎችን ትብብር ሲጠይቅ ከርሟል። ጋዜጠኛ ሔኖክ ስዩም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ፓርኮቿን ለመጠበቅ ቸልተኛ ሆናለች ሲል ይወቅሳል።

ዘገባዎቹን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ