1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብአዊ መብት መታሰቢያ ዕለትና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 2 2007

ዛሬ የኖቤል መሥራች አልፍረድ ኖቤል የሞተበት ዕለት መታሰቢያ ሲሆን የሚታሰበውም ለዓለም ሰላም ጉልሕ አስተዋጽዎ ለሚያደርግ ለሚያደርጉ የኖቤል የሰላም ሽልማት በመሰጠት ነው። የሚሰጠውም በኖርዌይ መዲና በኦስሎ ሲሆን ፤በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች ፤ ውጤታማ ለሆኑ ድግሞ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ ነው ሽልማቱ የሚሰጠው።

https://p.dw.com/p/1E2HH
Äthiopien - Internationaler Menschenrechtstag 2014
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

ይህ ቀን ማለት እ ጎ አ ታኅሳስ 10 ቀን በተጨማሪ ፤ ከ 195 0 ዓ ም አንስቶ በተባበሩት መንግሥታት አጠቃላይ ጉባዔ በተወሰነው መሠረት የሰብአዊ መብት መታሰቢያ ዕለት ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን፤ ሀገራት በመላ በገቡት ቃል መሠረት ሰብአዊ መብትን በየዕለቱ ዓመቱን ሙሉ እንዲያከብሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ፤ የዓለም ሕዝብ መንግሥቶቻቸውን በኀላፊነት እንዲጠይቅቁ ጥሪዬን አሰማለሁ ሲሉ መናገራቸው ተጠቅሷል።

በተለይ አዲስ አበባ ከተማ በሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችና የሴቶች ጥቃት ፖሊሶችና የሕግ ተርጓሚዎች ተገቢዉን ድጋፍ እንደማያደርጉ ይባስ ብለዉም ወንጀሉን የሚያባብሱ ተግባራት እንደሚፈጽሙ ተገለጸ። ይህ የተገለፀዉ ቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ለዴሞክራሲ የተሰኘዉ ድርጅት ዛሬ በኮከበ ፅባህ ት/ቤት አዳራሽ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀንን ሲያከብር ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ነዉ። ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶች በብሔራዊ ደረጃ በአሶሳ ከተማ መከበሩን ዘጋቢያን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር በላከልን ዘገባ አመልክቷል።

Äthiopien - Demonstration in Addis Abeba
ምስል DW

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ እየከፋ መምጣቱን ዓለም ዓቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዉማን ሪይትስ ዎች አስታዉቋል። የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት ይዞታ በተመለከተ የHRW የምሥራቅ አፍሪቃ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ማብራሪያ ሰጥተውናል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፣ ለዘንድሮው 2014 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት መታሰቢያ ዕለት ያቀረበው መፈክር ፤ « ሰብአዊ መብት 365» የተሰኘ ነው። ሰብአዊ መብት 365 የተሰኘው መፈክር ፍሬ ሐሳብ ምንድን ነው ፤ የ HRW የምሥራቅ አፍሪቃ የሰባአዊ መብት ይዞታ ተመልካች የሆኑት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሌስሊ ሌፍኮቭ-

«እንደሚመስለኝ ይህ መፈክር ሰብአዊ መብት 365፣ የሚያመላክተው በዓመት ውስጥ እያንዳንዱ ቀን የሰብአዊ መብት ቀን መሆኑን ነው። እ ጎ አ ታኅሳስ 10 ብቻ አይደለም። ምክንያቱም፣ ሰባአዊ መብት በመሠረቱ ከሰብእና ጋር የተያያዘ እያንዳንዱ ሰባአዊ ፍጡር በተፈጥሮ የታደለው ነው። እንዲሁ ሥጦታ ወይም የተለዬ ዕድል አይደለም። እያንዳንዱ ሰው ፣ በየዕለቱ ዓመቱን ሁሉ ያለው ሰባዓዊ መብቱ ነው። የመፈክሩ ዋና መልእክትም እንደሚመስለኝ ይህ ነው። »

በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ መንግሥት በተቃውሞ ፓርቲዎች ደጋፊዎች ሰልፍ ላይ የወሰደውን ርምጃ HRW ሳይታዘብ አልቀረም፤ አሁን ያለውን የኢትዮጵያን ሰባአዊ መብት አያኢዝ እርስዎ እንዴት ነው የሚገመግሙት? -

Human Rights Watch Logo Flash-Galerie
ምስል Human Rights Watch

«አሁን በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብአዊ መብት አያያዝ በጣም በጣም የሚያስጨንቅ ነው የሚመስለኝ። ባለፉት 10 ዓመት ያየነው ፤ በነጻ ሐሳብን መግለጽ የሚቻልበት ዕድል እንዳይኖር ያልተቋረጠ የማረቅ ርምጃ ሲካሄድ ነው። መገናኛ ብዙኀን ሆኑ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች(በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በማትኮር ይሠሩ የነበሩ የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶችን ማለት ነው) እንዲሁም ያለጥርጥር የተቃውሞ ወገኖች ድምፅም ነው የታፈነው።

በዚህ ዓመት እኮ ፣ እ ጎ አ በ 2014 የማረቁ እርምጃ እየተባባሰ መምጣቱን ዓይተናል። ለምሳሌ ያህል የ«ዞን 9 ጦማሪዎች» መያዝና ፍርድ ቤት መቅረብ፣ በዛ ያሉ ሕትመቶች መቋረጣቸው (መዘጋታቸው) የተለያዩ ማሕበረሰቦችየተቃውሞ ሰልፍ ሂደት ላይ የተደረገ የማጋጃ ርምጃ ፤ ይህ ሁሉ፤ በዚህ ዓመት ጭቆናው ይበልጥ ማየሉንየሚያሳይ ይመስለኛል። ይህም እጅግ የሚያስደነግጥ ነው። ሁኔታዎች አምና ከነበረው አስከፊ ሁኔታ ዘንድሮ ይበልጥ አስከፊ ወደ ሆነ ይዞታ ነው የተሸጋገሩት።»

የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና የመንግሥታቸው ከፍተኛ ሹማማንት ባለፈው ሳምንት በርሊን ፣ ጀርመን ውስጥ ከመራኂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልና ከመንግሥታቸው ባለሥልጣናት ጋር በጋራና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሲመካከሩ የሰብአዊ መብት ተገቢው ትኩረት የተሰጠው አልመሰለም። HRW ምን ይላል?----

ተክሌ የኋላ

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ