1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብአዊ መብት ድንጋጌ 60ኛ አመትና የአለም እዉነት

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 6 2001

ሰዉ እኩል ከሆነ፥ መብት ሰብእናዉ እኩል እንዲከበርለት ካስፈለገ የሚጣረስ ፍትሕም ሊኖር አይገባም።

https://p.dw.com/p/GGcm
ጉባኤዉምስል picture-alliance/dpa
የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት ባለፈዉ ሐሙስ ይፋ ያደረገዉ ዘገባ ብዙ የተጠይቁ ብዙ ያጠራጠሩ ሐቆች ዳግም እንዲጠየቁ፣ እንዲያነጋግሩ ምክንያት፣ ከመሆኑ እኩል፣ ሐይለኞች የኤሎኖር ሩዘቬልትን ትልም፣ የብጤዎቻቸዉን ፍላጎት፣ የግፉአንን ምኞት ሊያዳፍኑት እንጂ ሊያጠፉት እንደማይቻላቸዉ ትንሽ ግን ወቅታዊ እማኝ ነዉ።በአቡ-ግራይብና በዃንታናሞ እስረኞች ላይ ለተፈፀመዉ ዘግናኝ ግፍ የቀድሞዉ የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ተጠያቂ መሆናቸዉ ሐሙስ ይፋ ከመሆኑ በፊት ሮብ አለም ከሰብአዊ መብት ፅንሰ-ሐሳብ ጋር የተዋወቀበትን ስልሳኛ-አመት በተስፋ-ቀቢፀ ተስፋ መልዕክት አክብሯል።በአሉ መነሻ፣ መልዕክቱ፣ ማጣቃሻ ዘገባዉ አብነት፣ የአለም እዉነት መድረሻችን ነዉ።ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።