1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብዓዊ መብት ይዞታ በዚምባብዌ

ሰኞ፣ ኅዳር 29 2001

በዚምባብዌ እያደገ በመጣው ድህነት የተነሳ የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሶዋል።

https://p.dw.com/p/GBiW
የኃይሉ ተግባር ሰለባ
የኃይሉ ተግባር ሰለባምስል Thomas Kruchem
የዋጋ ግሽበቱ ባለፈው ነሀሴ አስራ አንድ ሚልዮን ከመቶ ተመዝግቦዋል። ህዝቡ ዳቦና ቅቤ የመግዛት አቅም የለውም፡ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ሰበብም ህዝቡ ወደጎረቤት ሀገሮች ተሰዶዋል። አምባገነኑ ፕሬዚደንት ሙጋቤ የሚመሩት ባለሙሉ ስልጣኑን ገዢውን ፓርቲ እና የተቃዋሚው ቡድን ስልጣን ለመጋራት የደረሱት ፖለቲካዊው ገላጋይ ሀሳብም እስካሁን በተግባር አልተተረጎመም። በሀገሪቱ የፖለቲካ ለውጥ እንዲደረግ የሚታገለውን በምህጻሩ WOZA በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የዚምባብዌ ሴቶችና ወንዶች ተነሱ የሚሰኘው መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት መስራች የሆኑት ጄኒ ዊልያምስ ባለፈው ወር የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሽልማት አግኝተዋል። ዊልያምስን የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ኡተ ሼፈር ሰሞኑን በበርሊን አነጋግቸዋለች።