1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ

Merga Yonas Bulaረቡዕ፣ ግንቦት 3 2008

የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማለት ሰቴት ዲፓርትመንት፤ ከትላንት በስትያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የዓለም አገሮች የሚታየዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ አዲስ ዘገባ አዉጥቷዋል።

https://p.dw.com/p/1IlrR
Oromo Proteste in Äthiopien
ምስል Oromia Media Network

[No title]

የዲፓርትመንቱ ጸሐፊ ጆን ኤፍ ኬር መንግስታቶች በስቪል ማኅበረሰብ ላይ የሚያሳድሩት ጫና እየጨመረ መምጣቱን፣ የመገናኛ ብዙኃን እና የኢንቴርኔት አገልግሎት የመጠቀም መብቶች መጥበባቸዉን፣ የተቃዋሚ ድምፆች መጨፍለቁን፣ ሠዎችን መግደል እና ከአገር እንዲወጡ ማዋከብ ዋነኛዉ መሆኑን መናገራቸዉ ዘገባዉ ያሳያል።


ኢትዮጵያን በተመለከተም በ40 ገፅ የተጠናከረዉ ዘገባ የሰብዓዊ እና የዲሞክራስያዊ መብቶች እየተባባሱ መምጣታቸዉን ያትታል። በተለይም ይላል ዘገባዉ የተቃዉም ፖለቲካ ፓርቲ አባል የሆኑትን እና ጋዜጠኞችን ማስፈራራት፣ ማሰር፣ መግረፍ እና ማሰቃየት፣ ከዛም አልፎ ያለምክንያት መግደልን ጨምሮ ሌሎች የሰባዊ መብት ጥሰቶች ሁሉ ይገኙበታል።


መቀመጫዉን ስቲክሆልም ስዊድን ያደረገዉ የሲቪል መብት ተሟጋች ፕሮጄክት ኃላፊ አቶ መስፍን ነጋሽ ዘገባዉ ከዚህ ቀደም በየዓመቱ ሲወጡ ከነበሩት ዘገባዎች በይዘቱም ሆነ በአቀራረቡ እንብዛም ልዪነት የለዉም ብለዋል። አቶ መስፍን በመቀጠል፣ ይህ የሚያሳየዉ አገሪቱ ዉስጥ ያለዉ የሰዎች መብት ይዞታ አለመሻሻሉን እና በአንድ አንድ ነገሮች ሁኔታዉ እየተባባሰ መምጣቱን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል። የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየዓመቱ ከሚያወጣዉ ዘገባ በዘለለ ምን መድረግ አለበት ለሚለዉ ጥያቄ ለዉጥ ከአሜርካ ሳይሆን ከማህበረሰቡ መሆኑን አቶ መስፍን ይናገራሉ።

አሜሪካ በራስዋ ማስጠበቅ የምትፈልገዉ ለሎች ቅድምያ የምትሰጠዉ ጥቅሞች እንዳሏት የምናገሩት አቶ መስፍን ዘገባዉ እንደ አንድ ምስክር በመዝገብ ተይዞ ሁሉም የራሱን ትግል እና ጥረት መቀጠል ይገባል ብለዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያን በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ መርዳቷ አገሪቱ ዉስጥ ያለዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ቀጥተኛ ተካፋይ ናት ብሎ የሚከሷት አልጠፉም። እንደዛም ሆኖ እንዲህ ያለ ዘገባ መዉጣቷ አቋሟን በትክክል የማታሳይ አድሎ የሚታይባት አሜሪካ ሲሉ ትችት የሚሰነዝሩ ጥቂቶች አይደሉም።


ኢትዮጵያ ከሚገኘዉ በአሜሪካ ኤምባሲ በኩል ዘገባዉን በተመለከተ ማብራራያ ለማገኘት ዛሬ ያደረግነዉ ተደጋጋሚ ጥረት ግን አልተሳካንም።

መርጋ ዮናስ


አዜብ ታደሰ