1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳኑ ፕሬዝዳት የአዲስ አበባ ጉብኝት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 14 2001

ፕሬዝዳት አል-በሽር እና የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ትናንት ማምሻ በጋራ እንዳሉት የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ብይን በሁለቱ ጎረቤት ሐገራት ግንኙነት ላይ የሚያሳድረዉ ተፅኖ የለም

https://p.dw.com/p/HcBH
ዑመር ሐሰን አል-በሽርምስል picture-alliance/ dpa

የሱዳኑ ፕሬዝዳት ኡመር ሐሰን አልበሽር በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ዛሬም እንደቀጠሉ ነዉ ።አለም አቀፉ ፍርድ ቤት የእስር ማዘዢያ ያወጣባቸዉ አልበሽር በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት አላማ በኢትዮ-ሱዳን የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ መካፈል ነበር።ፕሬዝዳት አል-በሽር እና የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ትናንት ማምሻ በጋራ እንዳሉት የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ብይን በሁለቱ ጎረቤት ሐገራት ግንኙነት ላይ የሚያሳድረዉ ተፅኖ የለም።አል-በሽር እንዲታሰሩ ከተበየነባቸዉ ወዲሕ ከኢትዮጵያ ሌላ ኤርትራን፥ግብፅን፣ ሊቢያንና ቀጠርን ጎብኝተዉ ነበር።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

Tadesse Engdaw/Negash Mohammed/Aryam Abraha

►◄