1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳንና የኢትዮጵያ መሪዎች ዉይይት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 26 2009

የሱዳኑ ፕሬዝደንት ዑመር ሐሰን አል በሽር እና የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ በጋራ እንዳስታወቁት ሱዳን፤ ሐዲዱ የሚዘረጋበትን መሬት ፈቅዳለች።በሁለቱ ሐገራት መካከል ነፃ የንግድና የምጣኔ ሐብት ቀጠና ለመመስረት ማቀዳቸዉንም መሪዎቹ አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/2agNM
Kigali Omar Bashir AU Gipfel
ምስል picture-alliance/dpa/P.Siwei

(Q&A) Al bashir in Äthiopien - MP3-Stereo

ኢትዮጵያን ከሱዳን የባሕር ወደብ ፖርት ሱዳን ጋር የሚያገናኝ የባቡር ሐዲድ ለመዘርጋት ሁለቱ መንግሥታት መስማማታቸዉን የሁለቱ ሐገራት መሪዎች አስታወቁ።ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ የተነጋገሩት የሱዳኑ ፕሬዝደንት ዑመር ሐሰን አል በሽር እና የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ በጋራ እንዳስታወቁት ሱዳን፤ ሐዲዱ የሚዘረጋበትን መሬት ፈቅዳለች። በሁለቱ ሐገራት መካከል ነፃ የንግድና የምጣኔ ሐብት ቀጠና ለመመስረት ማቀዳቸዉንም መሪዎቹ አስታዉቀዋል። የሁለቱን መሪዎች ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለዉ ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስን

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ