1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን እና ሊቢያ ፖለቲካዊ ቀውስ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 10 2011

የሰሜን ምስራቅ አፍሪካ አገሮቹ ሱዳን እና ሊቢያ ዛሬም በፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ናቸው። ሊቢያ በጎርጎሮሳዊው በ2011 ዓም ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ ከስልጣን ከተወገዱ ጀምሮ ሱዳን ደግሞ ባለፈው ወር መጀመሪያ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በህዝብ ከወረዱ ወዲህ ሰላም አላገኙም። 

https://p.dw.com/p/3IiP9
Sudan Proteste in Khartum
ምስል Reuters/M.N. Abdallah

የሱዳን እና ሊቢያ ፖለቲካዊ ቀውስ

ለሶስት አስርት ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩትን ኦማር አልበሽርን በአደባባይ ተቃውመው ከስልጣን ያስወገዱት ሱዳናውያን ገና ወደቤታቸው አልገቡም። እርሳቸውን ተክቶ ስልጣን የተቆጣጠረውን ወታደራዊውን ቡድን በሲቪል አስተዳደር እንዲተካ ለማድረግ ትግሉ አሁንም ቀጥሏል። 

የተቃውሞ መሪዎች እና ወታደራዊ ቡድን ለሶስት ዓመታት የሚቆይ የሽግግር መንግስት ለመመስረት የተስማሙ መሆኑን ባለፈው ረቡዕ ከገለጹ በኋላ በማግስቱ ሐሙስ የወታደራዊ ምክር ቤት መሪ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ቀርበው ድርድሩ ለ72 ሰዓታት ተቋርጧል ማለታቸው ብዙዎችን ግራ አጋብቷል። በተቃዋሚዎች እና ወታደራዊ ቡድኑ የሚካሄደው ድርድር የደረሱበትም ስምምነት ለሱዳን የዲሞራሲ ግንባታ ጥሩ ጅምር ሊሆን ይችላል የሚሉ ኃይሎች ድርድሩ ለጊዜውም ቢሆን ተቋረጠ መባሉ ስጋት አጭሮባቸዋል። 

በሽግግር መንግስቱ እና አመሰራረቱ ላይ ወታደራዊው ምክር ቤት አንድ አይነት አቋም እንደሌለው የሚገመት ሲሆን ካለፈው ስርዓት ጋር በተያያዘ በወንጀል ሊጠየቁ የሚችሉ የምክር ቤቱ አባላት በሂደቱ ደስተኞች እንዳልሆኑ ነው የሚነገረው። ሳዑዲ አረቢያ እና አጋሮቿም በሚቋቋመው የሽግግር መንግስት ወታደራዊ ምክር ቤቱ ቁልፍ ቦታ እንዲኖረው እና ከሱዳን ጋር የነበረው ወታደራዊ ግንኙነት አስተማማኝ እንዲሆን ይፈልጋሉ። 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ ። 

ገበያው ንጉሴ 

ተስፋለም ወልደየስ