1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን የምርጫ ዘመቻ

ዓርብ፣ የካቲት 5 2002

በሱዳን የምርጫ ዘመቻ በነገው ዕለት በይፋ ይጀመራል ። ምርጫው የሚካሄደው የፊታችን ሚያዚያ 3, 2002 ዓ.ም ነው ። ሆኖም በሱዳን የመምረጥ መብት ያለው 16 ሚሊዮን ህዝብ በሙሉ በርግጥ ድምፁን መስጠት መቻሉን በዚህ ወቅት ላይ ማንም እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይችልም ።

https://p.dw.com/p/Lzl7

የካርቱም መንግስትና የያኔው አማፂ የሱዳን ህዝብ ነፃ አውጭ ንቅናቄ በእንግሊዘኛው ምህፃር SPLM የ21 ዓመቱን የርስ በርስ ጦርነት ባስቆመው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት በተፈራረሙት ውል መሰረት የሚካሄደው የሚያዚያው ምርጫ ታሪካዊ ነው ። በዚህ ምርጫ በመላ ሱዳን የሚገኙ ዜጎች ከ24 ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የአካባቢ እና የብሄራዊ ምክር ቤት ዕንደራሴዎቻቸውን እንዲሁም ፕሬዝዳንታቸውን ይመርጣሉ ። ተጣምረው ሀገሪቱን የሚመሩት ሁለቱ ወገኖች ከምርጫው አስቀድሞ በአንዳንድ ህግጋት ሲነታረኩ ነበር ። ታዲያ ምርጫው በሚካሄድበት ወቅት በሱዳን ሰላም እንደሰፈነ ይቀጥል ይሆን ?

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ