1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን የሰላም ድርድር በአዲስ አበባ

ዓርብ፣ ኅዳር 10 2008

በሱዳን፤ ዳርፉር፣ ብሉናይልና ደቡብ ኮርዶፋን ግዛቶች ውስጥ እየተካሄደ ያለዉን ግጭት ለመግታት በአፍሪቃ ኅብረት ስር የሚገኝ የሸምጋዮች ቡድን አዲስ አበባ ላይ ድርድር እያካሄደ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1H9iQ
Bildergalerie Millionäre Afrika - AU Conference Center
ምስል picture-alliance/Zuma Press

[No title]

የሱዳንን መንግሥትና የተቀናቃኝ ኃይላቱን ተወካዮች እንዲሁም አደራዳሪዎዉ የደቡብ አፍሪቃዉ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ታቦ ምቤኪ ለተኩስ አቁም ድርድሩ ለሁለተኛ ቀን ዛሬ ስብሰባ መቀመጣቸዉ ታዉቋል። አዲስ አበባ ላይ የጀመረዉና በሱዳን የሰላም ስምምነት ላይ የሚመክረዉ ቡድን ሰብሳቢ የቀድሞዉ የናይጄርያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጎ ኦባሳንጆ መሆናቸዉ ታዉቋል። የሰላም ድርድሩን የተከታተለዉ የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ