1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን ጉባዔ በዋሽንግተን

ረቡዕ፣ ሰኔ 17 2001

በሰሜን እና በደቡብ ሱዳን መካከል ከአራት ዓመት በፊት የተፈረመውን የሰላም ውል ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማስደረግ የሚረዳ አንድ ትልቅ ጉባዔ በትናንትናው ዕለት በዋሽንግተን ተካሄደ።

https://p.dw.com/p/IYCx
ዚ,ሰላሙ ውል ከአራት ዓመት በፊት በተፈረመበተ ጊዜምስል AP

የዩኤስ አሜሪካ መስተዳድር ለሱዳን ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለማስገኘት ሁሉም የሚመለከታቸው ወገኖች የየበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጠይቆዋል። በዚሁ የደቡብ የሱዳን ህዝብ እንቅስቃሴና የሰሜኑ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ በዋነኛ ታዳሚነት በተጋበዙበትና ትልቅ ግምት በተሰጠው ጉባዔ ላይ የሰላሳ ሁለት ሀገሮችና ድርጅቶች ተወካዮች ተሳታፊዎች ነበሩ።

አበበ ፈለቀ/አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

AFA/AA