1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን ፕሬዚደንት ሀሰን አል በሺርና የእስራቱ ትዕዛዝ ዕቅድ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 5 2000

ዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የእስር ማዘዣ ለማዘጋጀት ማቀዱን

https://p.dw.com/p/Eb72
ፕሬዚደንት ኦማር ሀሰን አል በሺር
ፕሬዚደንት ኦማር ሀሰን አል በሺርምስል AP

አንድ የአሜሪካን ጋዜጣ አስታወቀ። ዋሽንግተን ፖስት የተባለው ጋዜጣ እንደዝገበው የዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሉዊስ ሞሬኖ ኦካምፖ ይህን ዕቅዳቸው የፊታችን ሰኞ ነው ለፍርድ ቤቱ የሚያቀርቡት። ሱዳን የኦካምፓን ዕቅድ በእሳት መጫወት ብላዋለች ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱዳን አምባሳደር አብደል መሀመድ አብደል ሀሊም ሞሀመድ ዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት በአልበሽር ላይ ያቀደው ክስ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የዳርፉር የሰላም ሂደት ያጠፋል ሲሉም አክለዋል።