1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን ፖለቲካዊ ቀዉስ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 16 2014

ፀጥታ አስከባሪዎች ሰልፈኛዉን በኃይል ለመበተን በወሰዱት እርምጃ በ10 የሚቆጠሩ ሰዎች መግደል፣ በመቶ የሚቆጠሩ ማቁሰላቸዉ ተዘግቧል።የተለያዩ ማሕበራትና መንግሥታት መፈንቅለ መንግስቱን አዉግዘዋል።

https://p.dw.com/p/42D1h
Sudan Putsch Protest Ausschreitungen
ምስል AFP/Getty Images

የሱዳን መፈንቅለ መንግስትና የገጠመዉ ተቃዉሞ

              

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄኔራል አብዱልፈታሕ አል ቡርሐን ትናንት ያደረጉትን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም የሐገሪቱ ሕዝብ የሚያደርገዉ የአደባባይ ሰልፍና አድማ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ፀጥታ አስከባሪዎች ሰልፈኛዉን በኃይል ለመበተን በወሰዱት እርምጃ በ10 የሚቆጠሩ ሰዎች መግደል፣ በመቶ የሚቆጠሩ ማቁሰላቸዉ ተዘግቧል።የተለያዩ ማሕበራትና መንግሥታት መፈንቅለ መንግስቱን አዉግዘዋል።የተባበሩት መንግስታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤትም ዛሬ በሱዳን ፖለቲካዊ ቀዉስ ላይ እየተነጋገረ ነዉ።

ገበያዉ ንጉሴ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ