1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲዊዘርላድ ሕዝበ ዉሳኔና አፃፋዉ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 22 2002

እርምጃዉ ሙስሊሞችን ቅር ሲያሰኝ፥የእምነት ነፃነትን እንደ መሠረታዊ የሰዉ ልጅ መብት የሚያዩ ወገኖችን ትችት ወቀሳ አስከትሏል።

https://p.dw.com/p/Kn8P
ምስል AP

ከባንክ አሠራር-አገልግሎቷ ጥቅም-ሐሜት ጋር በሰአት-ሥራ ዉበቷ ሥሟ የሚጠራዉ ስዊዘርላንድ ካለፈዉ እሁድ ወዲሕ ሐይማኖትን አቻችላ-የማኖር አቅም-ብልሐትዋ፥ የእምነት ነፃነትን የማክበር ፍላጎትዋ ብዙ ያነጋግር-ያከራክርም ይዟል።የሐገሪቱ ሕዝብ ባለፈዉ እሁድ በሰጠዉ ድምፅ ሚናሬት፥ ቁባ ወይም ጉልላት ያለዉ መስጊድ እንዳይሰራ የሚከለክለዉን ሐሳብ ደግፏል።እርምጃዉ ሙስሊሞችን ቅር ሲያሰኝ፥የእምነት ነፃነትን እንደ መሠረታዊ የሰዉ ልጅ መብት የሚያዩ ወገኖችን ትችት ወቀሳ አስከትሏል።

ሐይነር ኪዘል

ይልማ ኃ/ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ