1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ መራጮች ምዝገባ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 26 2012

ዛሬ ይጀመራል ተብሎ የታሰበው ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምፅ ሰጪዎች ምዝገባ ወደነገ መገፋቱ ተሰማ። ምዝገባው የተገፋው ለዚሁ ተግባር የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በአንዳንድ አካባቢዎች ስላለደረሰ መሆኑን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ለዶቼ ቬለ DW ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3SZxO
Äthiopien Stadtansicht Awassa
ምስል DW/S. Wegayehu

«ምዝገባው ነገ ይጀመራል»

ዛሬ ይጀመራል ተብሎ የታሰበው ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምፅ ሰጪዎች ምዝገባ ወደነገ መገፋቱ ተሰማ። ምዝገባው የተገፋው ለዚሁ ተግባር የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በአንዳንድ አካባቢዎች ስላለደረሰ መሆኑን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ለዶቼ ቬለ DW ገልጸዋል። በሌላ በኩል  የሲዳማ ብሄር ወደ ነጻነት የሚያደርገውን ሽግግር ለማሳካት በህዝበ ውሳኔው በነቂስ ውጥቶ አንዲመዘገብ ሲሉ የሲዳማ ዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ጥሪ አቅርበዋል ። ዋና አስተዳዳሪው አቶ ደስታ ሌዳሞ ዛሬ በሀዋሳ ሚሊኒየም አደባባይ ለድጋፍ ለተሰበሰቡ ነዋሪዎች እንዳሉት የሲዳማ ህዝብ ራሱን በክልል ለማደራጀት በተለያየ ጊዜ ሲያቀርብ የነበረው ጥያቄ የመጨረሻ ምላሽ የሚያገኝበት ላይ ደርሷል ብለዋል።  የሀዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ