1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲዳማ ሴቶች የሲዳማ ህዝብ በክልል እንዲደራጅ ጠየቁ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 1 2011

የሲዳማ ህዝብ ራሱን በክልል ለማደራጀት የተጠራው ህዝበ ውሳኔ በአፋጣኝ ገቢራዊ እንዲሆን የብሄረሰቡ ሲቶች ዛሬ ሀዋሳ ላይ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ። ሰልፈኞቹ በከተማዋ በሚገኙ ጎዳናዎች በመውጣት "ጥያቄያችን ሕገ-መንግሥታዊ ትግላችን ሰላማዊ ነው " የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

https://p.dw.com/p/3GWac
Hawassa Äthiopien Frauen-Marsch
ምስል DW/S. Wegayehu

ጥያቄያችን ሕገ-መንግሥታዊ ትግላችን ሰላማዊ ነው

 

በሰልፉ ላይ የተገኙት የከልሉ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በበኩላቸው ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት ያለውን የክልል መዋቅር ጥያቂ ተፈዳሚ ለማድረግ ከጎናቸው በመሆን አስፈላጊውን ድጋፈ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።  በተለይም የደቡብ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በበኩላቸው  ህዝቡ ያቀርበው ጥያቂ ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ የጀመረውን ትግል የአካባቢውን ሰላም በመጠበቀ ጭምር እንዲያካሂድ ጠይቀዋል።

Hawassa Äthiopien Frauen-Marsch
ምስል DW/S. Wegayehu

በደቡብ ክልል ከሲዳማ ጨምሮ በዞን መዋቅር በመተዳደር ላይ የሚገኙ አስራ አንድ ብሔረሰቦች ራሳቸውን በክልል ደረጃ ለማዋቀር የሚያስችላቸውን ጥያቂዎች ማቅረባቸው ይታወሳል። ክልሉን በገዢ ፓርቲነት የሚመራው የደቡብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቂ ደኢህዲን / የክልል መዋቅር ጥያቂዎቹን የህዝቦችን ትስስር በማይበጣጥስ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለኝን ጥናት እያካሂድኩ ነው ሲል በቅርቡ ማስታወቁ አይዘነጋም። የሰልፉን ሂደት የተከታተለው የሀዋሳው ዘጋቢያችን ተከታዩን ዘገባ አድርሶናል።

Hawassa Äthiopien Frauen-Marsch
ምስል DW/S. Wegayehu

ሽዋንግዛው ወጋየሁ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ