1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ወቅታዊ መግለጫ

ሐሙስ፣ የካቲት 21 2011

የደቡብ ክልልን በገዢ ፓርቲነት የሚያስተዳድረው የደቡብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ዴሞክሪያሲያዊ ንቅናቄ «ደኢህዴን» በህገ መንግሥታዊ የመብት ጥያቄዎች ላይ የሚደርገው ጣልቃ ገብነት የሥረዓት ለውጡን ጥያቄ ውስጥ እየከተተው ይገኛል ሲል የሲዳማ አርነት ንቅናቄ «ሲአን» አስታወቀ፡፡

https://p.dw.com/p/3EGjk
Äthiopien PK Sidama Libration Movmenet in Hawassa
ምስል DW/S. Wegayehu

የደቡብ ክልልን በገዢ ፓርቲነት የሚያስተዳድረው የደቡብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ዴሞክሪያሲያዊ ንቅናቄ «ደኢህዴን» በህገ መንግሥታዊ የመብት ጥያቄዎች ላይ የሚደርገው ጣልቃ ገብነት የሥረዓት ለውጡን ጥያቄ ውስጥ እየከተተው ይገኛል ሲል የሲዳማ አርነት ንቅናቄ «ሲአን» አስታወቀ፡፡ የንቅናቄው አመራሮች ዛሬ በወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ በሀዋሳ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሲዳማ ህዝብ ለረጅም ጊዜ የታገለለትን አራስን በእራስ የማስተዳደር ጥያቄ ይመልሳል የተባለውን ህዝበ ውሳኔ ተፈጻሚ ለማድረግ እየጠበቀ ይገኛል ብለዋል፡፡   

በሲዳማ አርነት ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ በአቶ ደሳለኝ ሜሳ የተነበበው የንቅናቄው መግለጫ ባለፉት ዓመታት የነበረው ጭቆና የዜጎችን ክብርና ሕይወት ከቀጠፈ በኋላ ብዙዎች በከፈሉት መስዋትነት አንጻራዊ ለውጥ መታየት ጀምሯል ብሏል፡፡

 ይሁንእንጂ ይህ የለውጥ ጅምር ክልሉን በገዢ ፓርቲነት በሚያስተዳድረው የደቡብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ዴሞክሪያሲያዊ ንቅናቄ «ደኢህዴን» በአስፈጻሚ ተቋማት ላይ እያደረገ በሚገኘው ጣልቃ ገብነት የተነሳ ለውጡ አደጋ ላይ እየወደቀ ይገኛል ሲልም አትቷል፡፡   የሲዳማ ህዝብ ለረጅም ጊዜ የታገለለትን አራስን በእራስ የማስተዳደር ጥያቄ ይመልሳል የተባለውን ህዝበ ውሳኔ ተፈጻሚ ለማድረግ እየጠበቀ እንደሚገኝ የጠቀሰው የንቅናቄው መግለጫ ውሳኔውን ተፈጻሚ ለማድረግ በደቡብ ክልል ምክር ቤት በኩል የቁርጠኝነት ማነስና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ይሳተዋላል ብሏል ፡፡

Kafeeernte in Äthiopien
ምስል Reuters/M. Haileselassie

በአገሪቱ ህገ መንግሥት መሠረት የደቡብ ክልል ምክር ቤት ህዝበ ውሳኔውን እንዲያደራጅ የተጠየቀው የንቅናቄው መግለጫ  የውሳኔ ሂደቱ እንዳይደናቀፍ የክልሉ የህግ አውጭውና የአስፈጻሚው አካላት የየራሳቸውን ሃላፊነት ብቻ እንዲፈጽሙም አሳስቧል፡፡ በቅርቡ የሚካሄደው አራተኛው አገር አቀፍ የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ከዚህቀደም እንደነበረው የሲዳማ ዞንን እና የሀዋሳ ከተማን በሚነጣጥል መልኩ ሊካሄድ አይገባም ያለው የንቅናቄው መግለጫ  ቆጠራውን የሚያስፈጽመው አካል ጉዳዩን ከወዲሁ እንዲያጤነው ሲልም ጠይቋል፡፡   የንቅናቄውን መግለጫ ተከትሎ ለአመራሮቹ ከጋዜጠኞች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል ፡፡   ከተነሱት ጥያቄዎች መካካል በህዝበ ውሳኔው ዙሪያ ህዝቡን በመወያየት ምን ያህል ግንዛቤ ፈጥራችኋል። ህዝበ ውሳኔውን አጓቷል ምትሉት የትኛው የመንግሥት አካል ነው፤ የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡   በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ የንቅናቄው ሊቀመንበት አቶ ዱካሌ ላሚሶ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡ ደቡብ ክልል የሚገኙ የዞን መስተዳድሮች  ከቅርብ ወራቶች ወዲህ እራሳቸውን በክልል መዋቅር ለመደራጀት የሚያስችሏቸውን ጥያቄዎች እያቀረቡ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

 ክልሉን በገዢ ፓርቲነት የሚያስተዳድረው የደቡብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ዴሞክሪያሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን)  እየቀረቡ የሚገኙ የክልል መዋቅር ጥያቄዎችን ድርጅቱ ባስቀመጠው አቅጣጫ ተፈጻሚ እንደሚያደርግ ባለፈው ሰኞ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ