1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲፒጄ ሽልማት ለኢትዮዽያዊው ጋዜጠኛ

ዓርብ፣ መስከረም 28 2003

ዓለም ዓቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ የ2010 ተሸላሚ የሆኑ አራት ጋዜጠኞችን መርጧል። ከእነዚህም አንዱ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ባልደረባ ዳዊት ከበደ ነው።

https://p.dw.com/p/PZj7

ሲፒጄ በየዓመቱ የሚሰጠው ሽልማት ጋዜጠኞች በየሀገሮቻቸው የሚደርስባቸውን አፈናና እንግልት ተጋፍጠው በሙያቸው ጠንክረው የሚገኙትን ጋዜጠኞች ለማበረታት ነው። በዘንድሮው ሽልማት አራት ጋዜጠኞች የተመረጡ ሲሆን እነሱም ሞሀመድ ዳቫሪ ከኢራን፤ ላውሬኖ ማርኩዝ ከቬንዙዌላ፤ ናዲራ ኢሳዬቫ ከሩሲያ እንዲሁም ዳዊት ከበደ ከኢትዮዽያ ናቸው። የሲፒጄ የአፍሪካ ክፍል ኃላፊ ሞሀመድ ኬይታ እንደሚሉት ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በኢትዮዽያ መንግስት የሚደርስበትን በደልና ጫና ተቋቁሞ ለህዝቡ መረጃ የማድረስ ሙያዊ ዓላማው ገፍቶበታል። የጋዜጠኛ ዳዊት መሸለም በኢትዮዽያ ያለውን የፕሬስ ጭቆና በግልጽ ለማሳየት ይረዳል ብለዋል ኃላፊው። ጋዜጠኛ ዳዊት በበኩሉ ሽልማቱ የበለጠ መስዋዕትነት ከፊት እንደሚጠብቅ የሚመላክት ሲል ገልጾ በኢትዮዽያ ጋዜጠኞች ስም ሽልማቱን እንደሚቀበል ተናግሯል። ሽልማቱ በመጪው ህዳር ወር በኒው ዮርክ በሚዘጋጅ ስነስርዓት ለተሸላሚዎቹ ይሰጣል።

መሳይ መኮንን

አርያም ተክሌ