1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳውዲ አረቢያ ተመላሾች በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ሰኔ 19 2007

ከ 1 ዓመት ተኩል ገደማ በፊት የሳዑዲአረቢያመንግሥትኢትዮጵያዉያንንጨምሮሕገ-ወጥያላቸውን የዉጪዜጎች ማበረሩይታወሳል። በወቅቱም አረብ ሀገራት የሚገኙ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ከገቡ ከ 1 ዓመት ተኩል አለፋቸው? ለመሆኑ እነዚህ ስደተኞች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?

https://p.dw.com/p/1FnRq
Pakistan Hausmädchen
ምስል Imtiaz Ahmad

የሳውዲ አረቢያ ተመላሾች በኢትዮጵያ

በርካታ ወጣት ሴት ኢትዮጵያውያን ኑሮዋቸውን ለማሻሻል እና ጥሩ ክፍያ ለማግኘት ሲሉ በህጋዊ እና በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ ተሰደዋል።ይሁንና የሳዑዲአረቢያ መንግሥትከ 1 ዓመት ተኩል ገደማ በፊት በሀገሩ የሚገኙ ሕገ-ወጥ የሚላቸው የዉጪ ዜጎችን ሲያባርር፤ ወደ 140 000 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ለመሆኑ እነዚህ ስደተኞች በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?

ጌጤነሽ ማዜ እና ገነት ታደሰ ሁለት የሳውዲ ዓረቢያ ተመላሾች ናቸው።ሁለቱም አንድ ዓላማ ነበራቸው፤ በተቻለው አጋጣሚ ሁሉ ውጭ ሀገር ሰርተው ባገኙት ገንዘብ ራሳቸውን መቀየር እና ቤተሰባቸውን ማስተዳደር፤ ጌጤነሽ በቤት ሰራተኛነት አንድ ዓመት ከስድስት ወር ሪያድ ቆይታለች።ጌጤነሽ እና ገነት ከሌሎች ስምንት የሳውዲ ዓረቢያ ተመላሾች ጋር በመሆን በጋራ ነው የሚሰሩት። ለነዚህ የሳውዲ ተመላሾች መንግሥት በነፃ የንግድ ቦታ ሰጥቷቸዋል። ለስራቸው ማንቀሳቀሻም 100 ሺ ብር ከመንግሥት ተበድረዋል። የሳውዲ ተመላሾቹ ምግብ እያበሰሉ ፤ ትኩስ መጠጥ እያዘጋጁ ይሸጣሉ። ቢሆንም በኑሮዋቸው አሁንም ደስተኛ አይደሉም።

እንደ ገነት እና ጌጤነሽ በርካታ ሴት ኢትዮጵያውያን ከተቀጠሩበት ቤት ሸሽተው በህገ ወጥነት ተደብቀው ሰርተዋል፤ አሁንም እየሰሩ ይገኛሉ። ኢትዮጵያኑ አሁንም ድረስ በውጭ ሀገራት እየሰሩ የሚገኙት ፤ ሀገራቸው ውስጥ የሚያገኙት ክፍያ ባለመመጣጠኑ እንደሆነ የሳውዲ ተመላሾቹ ይናገራሉ።

Arbeitsbedingungen für Frauen Ethiopische Frau im Libanon bei der Arbeit
ምስል AP

ገነትም ትሁን ጌጤነሽ ከሌሎች የሳውዲ ተመላሾች ጋር ሲወያዩ ብዙም ተስፋ የሚሰጥ ነገር አይሰሙም፤ እንደውም ተመልሰው ወደ አረብ ሀገር የሄዱ ሰዎች ሁለቱም ያውቃሉ። ጌጤነሽም ቢሆን ለዚህ እድሏን እየተጠባበቀጥ ነው።

ከ 1 ዓመት ተኩል ገደማ በፊት የሳዑዲአረቢያ መንግሥት በሀገሩ የሚገኙ ሕገ-ወጥ የሚላቸውን የዉጪ ሀገር ዜጎች ሲያባርር፤ በኢትዮጵያ መንግሥት አማካይነት ሀገሪቷን ለቀው አዲስ አበባ የገቡት ፤ ጌጤነሽ ማዜ እና ገነት ታደሰ በአሁኑ ሰዓት ኑሮዋቸው በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስል ነግረውናል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ