1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳውዲ የምሕረት አዋጅ እና በዚያ አለፈቃድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን 

እሑድ፣ ሚያዝያ 15 2009

የሳውዲ ዐረቢያ መንግሥት በጎርጎርዮሳውያኑ የዘመን ቀመር በ2013 ዓም በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩ የዉጭ ዜጎችን ያለምንም ቅጣት እና እንግልት ከግዛቱ እንዲወጡ የሚያስችል የምሕረት አዋጅ አውጥቶ እንደነበር ይታወሳል። ለሰባት ወር ተራዝሞ የነበረው አዋጅ ቀነ ገደብ ካለፈ በኋላ የሳውዲ ፀጥታ ኃይላት ጠንካራ ርምጃ መውሰዳቸው አይዘነጋም።

https://p.dw.com/p/2bhye
Saudi Arabien Arbeiter kehren nach Äthiopien zurück
ምስል DW/S. Shiberu

የሳውዲ የምሕረት አዋጅ እና ኢትዮጵያውያን 

በዚያን ጊዜ በሳውዲ ይገኙ የነበሩ ብዙ  ኢትዮጵያዉያን  ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የፈለጉ  ሁሉ ሳይቀሩ ታድያ ትልቅ  ችግር ገጥሟቸው ነበር፣ ታስረዋል፣ ተንገላተዋል። የሳውዲ መንግሥት አሁን ከአራት ዓመት በኋላም በጎርጎርዮሳውያኑ የዘመን ቀመር  ባለፈው መጋቢት (29/03/2017) ተመሳሳይ የምሕረት አዋጅ አውጥቷል። ይኸው የሳውዲ መንግሥት የምሕረት አዋጅ ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ነው።  ሳውዲ ዐረቢያ «ከሕገወጥነት የነጻች ሀገር» የሚል መጠሪያ የሰጠችው የምሕረት አዋጅ  አንድ ወር ሊሆነው ጥቂት ቀናት ነው የቀሩት።

ከ37 ሚልዮኑ የሳውዲ ሕዝብ መካከል ሁለቱ ሚልዮን በሕገ ወጥ እንደሚኖር መዘርዝሮች ያሳያሉ።  በሳዑዲ በሕገወጥነት ይኖራሉ ከሚባሉት የውጭ ዜጎች መካከል ኢትዮጵያውያንም ይገኙባቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ በምሕረት አዋጁ በቀረበላቸው እድል እንዲጠቀሙበት በተደጋጋሚ ማስገንዘቢያ እየቀረበ ነው። በዚሁ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሂደናል። 

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ