1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳዑዲ አረቢያና የስዊድን ዉዝግብ

ዓርብ፣ መጋቢት 4 2007

የሳዑዲ መሪዎች የስቶክሆልምን እርምጃ ለመበቀል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሯ በአረብ ሊግ ጉባኤ ላይ ንግግር እንዳያሰሙ ሲያግዱ፤ በስቶኮሆልም የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደርንም ወደ ሐገራቸዉ ጠርተዋል።

https://p.dw.com/p/1EqOu
ምስል AFP/Getty Images/I. Znotins

ሳዑዲ አረቢያና ስዊድን ከዚሕ ቀደም በተፈራረሙት የንግድ ሥምምነት ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ ወደ ዲፕሎማሲያዊ ንትርክ ንሯል። ሁለቱ ሐገራት የዛሬ አስር ዓመት የተፈራረሙት የንግድ ስምምነት እንዳይራዘም የሲዊድን ምክር ቤት ወስኗል። ከዚሕም በተጨማሪ የሲዊድን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር የሳዑዲ አረቢያ መንግሥትን ሰብአዊ መብት ይረግጣል በማለት ተችተዋል። ዉሳኔ- ትችቱ የሪያድ ገዢዎችን አበሳጭቷል። የሳዑዲ መሪዎች የስቶክሆልምን እርምጃ ለመበቀል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሯ በአረብ ሊግ ጉባኤ ላይ ንግግር እንዳያሰሙ ሲያግዱ፤ በስቶኮሆልም የሳዑዲ አረቢያ አምባሳደርንም ወደ ሐገራቸዉ ጠርተዋል። የስቶክሆልሙ ወኪላችን ቴዎድሮስ ምሕረቱ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ቴዎድሮስ ምሕረቱ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ