1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳዑዲ አረቢያ ሕግና ኢትዮጵያዉን ስደተኞች

ነጋሽ መሐመድ
ዓርብ፣ ነሐሴ 12 2009

የቀነ ገደቡ ዳግም መራዝም የመጣው ይምጣ ብለው እዚያዉ ሳዑዲ አረቢያ የቀሩትን የዉጪ ዜጎች ለጊዜውም ቢሆን ያበረታታ፤ ሐገር ከገቡትም አንዳንዶቹን ያስቆጨ እና ዳግም እንዲሰደዱ ያበረታታ እንደሆነ እየተነገረ ነዉ

https://p.dw.com/p/2iSuH
Äthiopische Rückkehr
ምስል DW/S. Shibru

የሳዑዲ አረቢያ ሕግና ኢትዮጵያዉያን

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት «ሕገ-ወጥ የሚላቸዉ» የዉጪ ዜጎች ከሐገሩ እንዲወጡ የወሰነዉን ቀነ-ገደብ ለሁለተኛ ጊዜ ቢያራዝምም ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ የሚያመለክቱት ኢትዮጵያዉን ቁጥር  አነስተኛ ነዉ።የቀነ ገደቡ ዳግም መራዝም የመጣው ይምጣ ብለው እዚያዉ ሳዑዲ አረቢያ የቀሩትን የዉጪ ዜጎች ለጊዜውም ቢሆን ያበረታታ፤ ሐገር ከገቡትም አንዳንዶቹን ያስቆጨ እና ዳግም እንዲሰደዱ ያበረታታ እንደሆነ እየተነገረ ነዉ፡፡በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ሊቀመንበር ግን «ሀገርን ከህገወጦች ማንጻት» የሚል ስያሜ የተሰጠው የሳዑዲ አረቢያ ዘመቻ ይዋል ይደር እንጂ ተግባራዊ መሆኑ አይቀርም ይላሉ፡፡

ስለሺ ሽብሩ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ መለሰ