የሳዑዲ አረቢያ ምህረት
ማክሰኞ፣ የካቲት 19 2005ማስታወቂያ
የሳዑዲ አረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ ሣይኖራቸዉ ለቆዩ ምህረት አደረገ።በምህረቱ መሠረትም ያለመኖሪያ እና ስራ ፈቃድ ሳዉዲ የሚገኙ ወገኖች ያለምንም ቅጣትና እስራት ወደሀገራቸዉ እንዲመለሱ መወሰኑን የጄዳዉ ወኪላችን በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል። የሳዉዲ አረቢያ መንግስት ምህረትም በዚህ ሁኔታ እዚያ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያዉያንን አስደስቷል። ነቢዩ ሲራክ ጉዳዩ የሚመለከታቸዉን አነጋግሮ ዝርዝር ዘገባ አድርሶናል።
ነቢዩ ሲራክ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ