1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳዑዲ አረቢያ የምጣኔ ሐብት ተሐድሶ

ሐሙስ፣ ግንቦት 4 2008

የንጉስ ሠልማን ወንድ ልጅ የምክትል አልጋወራሽ መሐመድ ቢን ሠልማን የ«አዕምሮ ልጅ» የተባለዉ ዕቅድ የሐገሪቱ ዜጎች በተለያዩ የምጣኔ ሐብት መስኮች እንዲሳተፉ፤የዉጪ ባለሙያዎችን ተክተዉ እንዲሠሩ፤የሴቶች ተሳትፎ እንዲኖር እና ሐገሪቱ ለዉጪ ባለሐብቶች ክፍት እንድትሆን የሚያደርግ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1ImP5
ምስል Reuters/Saudi Press Agency

የሳዑዲ አረቢያ ነገሥታት የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብታዊ አቋም ለመለወጥ ይረዳል ያሉትን አዲስ ዕቅድ በቅርቡ ይፋ አድርገዋል።ራዕይ 2030 የተሰኘዉ ዕቅድ የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብት እስካሁን ካለበት ከነዳጅ ዘይት ጥገኝነት ለማላቀቅና የምጣኔ ሕብቱን ምንጭ ለማስፋት ያለመ ነዉ።የንጉስ ሠልማን ወንድ ልጅ የምክትል አልጋወራሽ መሐመድ ቢን ሠልማን የ«አዕምሮ ልጅ» የተባለዉ ዕቅድ የሐገሪቱ ዜጎች በተለያዩ የምጣኔ ሐብት መስኮች እንዲሳተፉ፤የዉጪ ባለሙያዎችን ተክተዉ እንዲሠሩ፤የሴቶች ተሳትፎ እንዲኖር እና ሐገሪቱ ለዉጪ ባለሐብቶች ክፍት እንድትሆን የሚያደርግ ነዉ።ዕቅዱን ገቢራዊ ለማድረግም የተለያዩ የሚንስቴር መስሪያ ቤቶች ባዲስ መልክ ተዋቅረዋል።የካቢኔ ሹም ሽር ተደርጓልም።የሪያድ ነዋሪ ሥለሺ ሽብሩን ሥለዕቅዱ በሥልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ሥለሺ ሽብሩ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ