1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳዑዲ ግብረ-ሠናይ ድርጅት ሆስፒታል በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 30 2007

ድርጅቱ ቀደም ሲል ሆስፒታሉን አዲስ አበባ ዉስጥ ለመገንባት ጥያቄ ቢያቀርብም የከተማይቱ መስተዳድር ለሆስፒታሉ ማስገንቢያ የሚሆን መሬት ባለመፍቀዱ ትግራይ ዉስጥ ለማስገንባት ወስኗል።

https://p.dw.com/p/1E1a0
ምስል DW/Getachew Tedla

አል ባስር የተሠኘ የሳዑዲ አረቢያ ግብረ-ሠናይ ድርጅት ሽሬ እንደ ስላሴ-ትግራይ ዉስጥ የዓይን ሕክምና መስጪያ ሆስፒታልና የሕክምና ባለሙያዎች ማሠልጠኛ ማዕከል ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አኖረ። ድርጅቱ ቀደም ሲል ሆስፒታሉን አዲስ አበባ ዉስጥ ለመገንባት ጥያቄ ቢያቀርብም የከተማይቱ መስተዳድር ለሆስፒታሉ ማስገንቢያ የሚሆን መሬት ባለመፍቀዱ ትግራይ ዉስጥ ለማስገንባት ወስኗል። ድርጅቱ ከትግራይ በተጨማሪ በኒ ሻንጉል፤ ሶማሊያ፤ ድሬዳዋና አፋር መስተዳድር ተመሳሳይ ሆስፒታሎች ለመገንባት አቅዷል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ